እንዲህም ሆነ፦ ይስሐቅ ፈጽሞ ከአረጀ በኋላ ዐይኖቹ ፈዝዘው አያይም ነበር። ታላቁን ልጁን ዔሳውንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
ዘዳግም 34:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይኖቹም አልፈዘዙም፤ ጕልበቱም አልደከመም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ዓመት ነበር፤ ሆኖም ዐይኑ አልፈዘዘም፤ ጕልበቱም አልደከመም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ፥ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጉልበቱም አልደነገዘም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ኻያ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን ዐይኑ ያልፈዘዘና ጒልበቱም ያልደከመ ገና ብርቱ ሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ዓመት ነበረ፤ ዓይኑ አልፈዘዘም፥ ጉልበቱም አልደነገዘም። |
እንዲህም ሆነ፦ ይስሐቅ ፈጽሞ ከአረጀ በኋላ ዐይኖቹ ፈዝዘው አያይም ነበር። ታላቁን ልጁን ዔሳውንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።
የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ከብደው ነበር፤ ማየትም አይችልም ነበር፤ ወደ እርሱም አቀረባቸው፤ ሳማቸውም፤ አቀፋቸውም።
በወራቱ የደረሰ አዝመራ እንዲሰበሰብ፥ የእህሉ ነዶም በወቅቱ ወደ አውድማ እንዲገባ፥ በረዥም ዕድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ።
“አርባ ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ በበረሃ በደብረ ሲና የእግዚአብሔር መልአክ በቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ታየው።
አላቸውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ‘ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል።
የእስራኤልም ልጆች በዮርዳኖስ በኢያሪኮ አቅራቢያ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።