ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።
ዘዳግም 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልን ሁሉ፣ አንተም አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክንሻገር ድረስ እንደዚሁ አድርግልን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላካችን ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ፥ በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች በዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አድርግልኝ።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኤዶም የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ የሞአብ ዘሮች በግዛታቸው በኩል እንድናልፍ እንደ ፈቀዱልን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረን እግዚአብሔር ወደሚያወርሰን ምድር እስክንገባ ድረስ በዚያ ለማለፍ ፍቀድልን።’ |
ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ ይህም ከአባቴ የወለድሁት ማለት ነው። እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
የኤዶምያስም ንጉሥ “በእኔ በኩል አታልፍም፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዋጋለን፤ በጦርም እቀበልህ ዘንድ እወጣለሁ” አለው።
እነሆ፥ ምድሪቱን ሰጠኋችሁ፤ ግቡ፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ምድር ውረሱ።
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር በለዓምን ይሰማ ዘንድ አልወደደም፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ወድዶሃልና ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠልህ።
አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ።
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
እግዚአብሔርም እናንተ በተናገራችሁት ምክንያት ተቈጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር፥ አምላክህም እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ።
እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ ዛሬ ዕወቅ።