ማልደውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፥ “ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢዩም እመኑ፤ ነገሩም ይቀናላችኋል” አለ።
ዘዳግም 1:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳሩ ግን በዚህ ነገር አምላካችሁ እግዚአብሔርን አላመናችሁትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሆኖ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልታመናችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ሆኖ በዚህ ነገር ጌታ አምላካችሁን አላመናችሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሆኖ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት ቀን በደመና ሌሊት በእሳት፥ በፊታችሁ በሚሄደው በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልተማመናችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን ለሰፈራችሁ የሚገባውን ስፍራ እንዲፈልግላችሁ፥ ትሄዱበት ዘንድ የሚገባውንም መንገድ እንዲያሳያችሁ ሌሊት በእሳት፥ ቀን በደመና በፊታችሁ በመንገድ ሲሄድ የነበረውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን በዚህ ነገር አላመናችሁም። |
ማልደውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፥ “ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢዩም እመኑ፤ ነገሩም ይቀናላችኋል” አለ።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስቈጡኛል? በፊታቸውስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምኑብኝም?
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ዕወቁ፤ ከእናንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይማኖት የጐደለውና ተጠራጣሪ፥ ከሕያው እግዚአብሔር የሚለያችሁ ክፉ ልብ አይኑር።
ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛም የምሥራች ተሰብኮልናል፤ ነገር ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።
ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብጽ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።