Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 1:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እር​ሱም ስፍ​ራን እን​ዲ​መ​ር​ጥ​ላ​ችሁ፥ ትሄ​ዱ​በ​ትም ዘንድ የሚ​ገ​ባ​ውን መን​ገድ እን​ዲ​ያ​ሳ​ያ​ችሁ ሌሊት በእ​ሳት፥ ቀን በደ​መና በፊ​ታ​ችሁ በመ​ን​ገድ ሲሄድ የነ​በ​ረ​ውን አላ​መ​ና​ች​ሁ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በጕዞ ላይ ሳላችሁ የምትሰፍሩባቸውን ቦታዎች ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት እርሱ ሌሊት በእሳት፣ ቀን በደመና ይመራችሁ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እርሱ ግን የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግ፥ ትሄዱበት ዘንድ የሚገባውንም መንገድ ለማሳየት ሌሊት በእሳት፥ ቀን በደመና በፊታችሁ በመንገድ ሲሄድ የነበረውን ጌታ አምላካችሁን አላመናችሁም።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 1:33
16 Referencias Cruzadas  

የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ታበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ቀን በደ​መና ዐምድ፥ ሌሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ መራ​ሃ​ቸው።


በሥ​ራ​ቸ​ውም ረከ​ሰች፥ በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውም አመ​ነ​ዘሩ።


ዓለ​ቱን ይመታ ዘንድ ውኃ​ንም ያፈስ ዘንድ ይች​ላ​ልን? እን​ጀ​ራን መስ​ጠ​ትና ለሕ​ዝ​ቡስ ማዕ​ድን መሥ​ራት ይች​ላ​ልን?”


ንጋ​ትም በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳ​ትና በደ​መና ዐምድ ሆኖ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንን ሠራ​ዊት ተመ​ለ​ከተ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት አወከ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከሰ​ይፍ የተ​ረ​ፈው ሕዝብ በም​ድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ሂዱ፦ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አታ​ጥፉ።”


በዚያ ቀን ከግ​ብፅ ምድር ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው፥ ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ት​በ​ልጥ ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አነ​ሣሁ።


እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተራራ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ተጓዙ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኪ​ዳኑ ታቦት የሚ​ያ​ድ​ሩ​በ​ትን ቦታ ታገ​ኝ​ላ​ቸው ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ትቀ​ድ​ማ​ቸው ነበር።


የዚ​ያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሕዝ​ብህ መካ​ከል እንደ ሆንህ ሰም​ተ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐ​ይን እን​ደ​ሚ​ተ​ያይ ተገ​ል​ጠ​ህ​ላ​ቸ​ዋል። ደመ​ና​ህም በላ​ያ​ቸው ቆመች። በቀ​ንም በደ​መና ዐምድ ፥ በሌ​ሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ በፊ​ታ​ቸው ትሄ​ዳ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos