La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም በአ​ን​ባ​ዪቱ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ተባ​ለች። ከተ​ማ​ዋ​ንም ዙሪ​ያ​ዋን እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ቀጠ​ራት፤ ቤቱ​ንም ሠራ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በዐምባዪቱ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ዳዊት መኖሪያውን በምሽጉ ላይ አደረገ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራው። ዳዊትም ከሚሎ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ገነባው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዳዊት ምሽጉን ከያዘ በኋላ መኖሪያውን በዚያው ስፍራ አደረገ፤ እርስዋንም “የዳዊት ከተማ” ብሎ ጠራት፤ ከኮረብታው በስተ ምሥራቅ በኩል በዐፈር ከተደለደለው ስፍራ አንሥቶ በኮረብታው ዙሪያ ከተማይቱንም ሠራ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም በአምባይቱ ውስጥ ተቀመጠ፥ የዳዊትም ከተማ ብሎ ጠራት። ዳዊትም ዙሪያዋን ከሚሎ ጀምሮ ወደ ውስጥ ቀጠራት።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 5:9
16 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ዳዊት አን​ባ​ዪ​ቱን ጽዮ​ንን ያዘ፤ እር​ስ​ዋም የዳ​ዊት ከተማ ናት።


በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​መታ ሁሉ፥ ዕው​ሮ​ች​ንና አን​ካ​ሶ​ችን፥ የዳ​ዊ​ት​ንም ነፍስ የሚ​ጠ​ሉ​ትን ሁሉ በሳ​ንጃ ይው​ጋ​ቸው” አለ። ስለ​ዚ​ህም፥ “ዕው​ርና አን​ካሳ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግቡ” ተባለ።


ዳዊ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመ​ጣት ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም፤ ዳዊ​ትም በጌት ሰው በአ​ቢ​ዳራ ቤት አገ​ባት።


እር​ሱም ያደ​ረ​ገው ይህ ነው በን​ጉሡ በሰ​ሎ​ሞን ላይ እጁን አነሣ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዳ​ርቻ ያለ ቅጥ​ር​ንና የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ከተማ ቅጥር ሠርቶ ጨረሰ።


ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና ቤተ መን​ግ​ሥ​ቱን፥ ሜሎ​ን​ንም፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቅጥር፥ አሶ​ር​ንም፥ መጊ​ዶ​ንም፥ ጋዜ​ር​ንም ይሠራ ዘንድ ሠራ​ተ​ኞ​ችን መል​ምሎ ነበር።


የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ ሰሎ​ሞን ወደ ሠራ​ላት ወደ ቤቷ አመ​ጣት፤ በዚያ ጊዜም ሚሎ​ንን ሠራት።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ዳዊ​ትም የከ​ተ​ማ​ዋን ዙሪያ ቀጸረ፤ ተዋ​ግ​ቶም እጅ አደ​ረ​ጋት።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።


የመ​ሴ​ፋም ገዢ የኮ​ል​ሐዜ ልጅ ሰሎም የም​ን​ጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደ​ነ​ውም፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ፤ ከዳ​ዊ​ትም ከተማ እስ​ከ​ሚ​ወ​ር​ደው ደረጃ ድረስ በን​ጉሡ አት​ክ​ልት አጠ​ገብ ያለ​ውን የመ​ዋኛ ቅጥር ሠራ።


ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፤ ስድ​ብን እጅግ ጠግ​በ​ና​ልና፤


ዳዊት ለሰ​ፈ​ረ​ባት ከተማ ለአ​ር​ኤል ወዮ​ላት! የዓ​መ​ቱን አዝ​መራ ሰብ​ስቡ፤ ከሞ​ዓብ ጋር ትበ​ላ​ላ​ች​ሁና።


እን​ዲህ ባይ​ሆን ግን ከአ​ቤ​ሜ​ሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰ​ቂ​ማ​ንም ሰዎች፥ የመ​ሐ​ሎ​ን​ንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይ​ሆን ከሰ​ቂማ ሰዎች ከመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ትብ​ላው።”


የሰ​ቂ​ማም ሰዎች ሁሉ፥ የመ​ሐ​ሎ​ንም ቤት ሁሉ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሄደ​ውም በሰ​ቂማ በዐ​ምዱ አጠ​ገብ ባለው የወ​ይራ ዛፍ በታች አቤ​ሜ​ሌ​ክን አነ​ገሡ።