2 ሳሙኤል 17:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርበውና ተጠምተው ደክመው ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማር፣ ርጎ፣ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፣ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሟል፤ ተጠምቷል” በማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማር፥ እርጎ፥ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፥ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሞአል፤ ተጠምቶአል” ብለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስንዴ፥ ገብስ ዱቄት፥ የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላ፥ ምስር፥ የተቆላ ሽንብራ፥ ማር፥ ቅቤ፥ በጎች፥ የላምም እርጎ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ አመጡላቸው። |
ንጉሡም ሲባን፥ “ይህ ለአንተ ምንድን ነው?” አለው። ሲባም፥ “አህዮቹ የንጉሥ ቤተ ሰቦች ይቀመጡባቸው ዘንድ፥ እንጀራውና ተምሩም ብላቴኖቹ ይበሉት ዘንድ፥ የወይን ጠጁም በበረሃ የሚደክሙት ይጠጡት ዘንድ ነው” አለ።
ደክሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለሁ፤ አስፈራውማለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፤ ንጉሡንም ብቻውን እገድለዋለሁ፤
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።