Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የሄ​ሮ​ድስ አዛዥ የነ​በ​ረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስ​ናም፥ በገ​ን​ዘ​ባ​ቸው ያገ​ለ​ግ​ሉት የነ​በሩ ብዙ​ዎች ሌሎ​ችም ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የሄሮድስ ቤት ኀላፊ የነበረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፣ ሶስና፣ ደግሞም ሌሎች ብዙዎች ነበሩ፤ እነዚህም በግል ንብረታቸው የሚያገለግሉት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የሄሮድስ መጋቢ የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስናና ብዙዎች ሌሎችም ሆነው ከንብረታቸው በመጠቀም ያገለግሉአቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የሄሮድስ ቤት አዛዥ የነበረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስናና ሌሎችም ብዙዎች ነበሩ፤ እነዚህ ሴቶች ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘባቸው ያገለግሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የሄሮድስ አዛዥ የኩዛ ሚስት ዮሐናም ሶስናም ብዙዎች ሌሎችም ሆነው በገንዘባቸው ያገለግሉት ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 8:3
19 Referencias Cruzadas  

ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


ቅዱ​ሳ​ንም ሁሉ፥ ይል​ቁ​ንም ከቄ​ሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


ንግ​ድ​ዋና ዋጋዋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል፤ ንግ​ድ​ዋም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለሚ​ኖሩ ለመ​ብ​ላ​ትና ለመ​ጠ​ጣት፥ ለመ​ጥ​ገ​ብም፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናል እንጂ ለእ​ነ​ርሱ አይ​ሰ​በ​ሰ​ብም።


ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


እነ​ዚ​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያም፥ ዮሐና፥ የያ​ዕ​ቆብ እናት ማር​ያም፥ አብ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩት ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ይህን ለሐ​ዋ​ር​ያት ነገ​ሩ​አ​ቸው።


በአ​ን​ጾ​ኪያ በነ​በ​ረ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም ነቢ​ያ​ትና መም​ህ​ራን ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም በር​ና​ባስ፥ ኔጌር የተ​ባ​ለው ስም​ዖን፥ የቀ​ሬ​ናው ሉቅ​ዮስ፥ ከአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ከሄ​ሮ​ድስ ጋር ያደ​ገው ምናሔ፥ ሳው​ልም ነበሩ።


በዚያ ዘመን የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ የኢየሱስን ዝና ሰማ፤


ሄሮድስ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ዮሐንስን አስይዞ አሳስሮት በወህኒ አኑሮት ነበርና፤


ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች፤ ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤


በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን ‘ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።


ኢየሱስን እያገለገሉ ከገሊላ የተከተሉት ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ሲመለከቱ በዚያ ነበሩ፤


ይህ​ንም ያለ፥ ድሆች አሳ​ዝ​ነ​ውት አይ​ደ​ለም፤ ሌባ ነበ​ርና፥ ሙዳየ ምጽ​ዋ​ቱ​ንም ሲጠ​ብቅ በው​ስጡ ከሚ​ገ​ባው ይወ​ስድ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ነው እንጂ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios