Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 17:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ማር፣ ርጎ፣ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፣ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሟል፤ ተጠምቷል” በማለት ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ማር፥ እርጎ፥ በጎችና የላም አይብ እንዲበሉ ለዳዊትና ለሕዝቡ አመጡላቸው፤ ይህን ያደረጉትም፥ “ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፤ ደክሞአል፤ ተጠምቶአል” ብለው ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳ​ዊ​ትና ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በም​ድረ በዳ ተር​በ​ውና ተጠ​ም​ተው ደክ​መው ነበ​ርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ስንዴ፥ ገብስ ዱቄት፥ የተጠበሰ እሸት፥ ባቄላ፥ ምስር፥ የተቆላ ሽንብራ፥ ማር፥ ቅቤ፥ በጎች፥ የላምም እርጎ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ አመጡላቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 17:29
15 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ሲባን፣ “ይህን ሁሉ ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሲባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተ ሰዎች እንዲቀመጡባቸው፣ እንጀራውንና በለሱን ወጣቶቹ እንዲበሉት፣ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው።


ለተጠሙ ውሃ አምጡ። በቴማን የምትኖሩ፣ ለስደተኞች ምግብ አምጡ።


ንጉሡና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ለመሄድ ወዳሰቡበት ስፍራ ደረሱ፤ በጣም ደክሟቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ።


ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


የሄሮድስ ቤት ኀላፊ የነበረው የኩዛ ሚስት ዮሐና፣ ሶስና፣ ደግሞም ሌሎች ብዙዎች ነበሩ፤ እነዚህም በግል ንብረታቸው የሚያገለግሉት ነበሩ።


ምግብህን ለተራበ እንድታካፍለው፣ ተንከራታቹን ድኻ ወደ ቤትህ እንድታስገባው፣ የተራቈተውን ስታይ እንድታለብሰው፣ የሥጋ ዘመድህንም ፊት እንዳትነሣው አይደለምን?


እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።


በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜም አደጋ እጥልበታለሁ፤ ሽብር እለቅበታለሁ፤ ከዚያም ዐብሮት ያለው ሕዝብ ሁሉ ትቶት ይሸሻል፤ ንጉሡን ብቻ እመታዋለሁ፣


ይህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፍ ለክፍል አዛዣቸው ዐብረህ ውሰድ፤ ወንድሞችህም እንዴት እንደ ሆኑ አይተህ፣ ደኅንነታቸውን የሚያረጋግጥ ምልክት ከእነርሱ ዘንድ አምጣልኝ።


ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።


ተራቡ፤ ተጠሙ፤ ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios