እነሆም፥ ንጉሡን እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር መዘምራንና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።
2 ነገሥት 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም በዓምደ ወርቁ አጠገብ ቆሞ እግዚአብሔርን ይከተሉ ዘንድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩንም ሥርዐቱንም በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ይጠብቁ ዘንድ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳን ጸኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም በዐምዱ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እግዚአብሔርን እንደሚከተል ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹን፣ ሥርዐቶቹን በፍጹም ልቡና በፍጹምም ነፍሱ እንደሚጠብቅ፣ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን ኪዳን እንደሚያጸና በእግዚአብሔር ፊት ኪዳኑን አደሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ቃል ኪዳን ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሓሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም በዐምደ ወርቁ አጠገብ ቆሞ እግዚአብሔርን ተከትሎ ይሄድ ዘንድ፥ ትእዛዙንና ምስክሩንም ሥርዐቱንም በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ ይጠብቅ ዘንድ፥ በዚሁም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል ያጸና ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፤ ሕዝቡም ሁሉ ቃል ኪዳን ገቡ። |
እነሆም፥ ንጉሡን እንደ ተለመደው በዓምዱ አጠገብ ቆሞ፥ ከንጉሡም ጋር መዘምራንና መለከተኞች ቆመው አየች፤ የሀገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከት ይነፉ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው፥ ዐመፅ ነው፥” ብላ ጮኸች።
ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ፥ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፤ ደግሞም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ።
በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው ዕረፍትን ሰጣቸው።
እነሆም፥ ንጉሡ በመግቢያው በዓምዱ አጠገብ ሆኖ በንጉሡም ዙሪያ አለቆችና መለከተኞች፥ መኳንንትም ቆመው አየች። ሕዝቡም ሁሉ ደስ ብሎአቸው መለከቱን ይነፉ ነበር፤ መዘምራንም በዜማ ዕቃ እያዜሙ የምስጋና መዝሙር ይዘምሩ ነበር። ጎቶልያም ልብስዋን ቀድዳ፥ “ዐመፅ ነው! ዐመፅ ነው!” ብላ ጮኸች።
አሁንም የቍጣውን መቅሠፍት ከእኛ እንዲመልስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን አደርግ ዘንድ በልቤ አስቤአለሁ።
አሁንም እንደ ጌታዬና የአምላካችንን ትእዛዝ እንደሚፈሩት ምክር፥ ሴቶችን ሁሉ፥ ከእነርሱም የተወለዱትን እንሰድድ ዘንድ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ። ተነሥ እንደ አምላካችንም ትእዛዝ ገሥፃቸው፤ እንደ ሕጉም ያድርጉ፤
ደግሞም ልብሴን አራገፍሁና፥ “ይህን ነገር የማያደርገውን ሰው ከቤቱና ከሥራው እንዲሁ እግዚአብሔር ያራግፈው፤ እንዲሁ የተራገፈና ባዶ ይሁን” አልሁ። ጉባኤውም ሁሉ፥ “አሜን” አሉ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ ሕዝቡም እንደዚህ ነገር አደረጉ።
ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ አለቆቻችንም፥ ሌዋውያኖቻችንም፥ ካህናቶቻችንም ያትሙበታል።”
ሙሴም ገባ፤ ለሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥርዐቱንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፥ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እንሰማለን፤ እናደርጋለንም” ብለው መለሱ።
እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዓመተ ኅድገትን በማድረግ በዐይኔ ፊት ቅን የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር፤ ስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።
ስለ አርነታቸው ዐዋጅ እንዲነግር ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ከአደረገ በኋላ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
ሕያው እግዚአብሔርን! ብሎ በእውነትና በቅንነት፤ በጽድቅም ቢምል፥ አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ፤ በኢየሩሳሌምም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።
ወደ ጽዮን የሚሄዱበትን ጎዳና ይመረምራሉ፤ ፊታቸውንም ወደ ሀገራቸው ይመልሳሉ፤ የዘለዓለም ቃልኪዳን አይረሳምና መጥተው ወደ ፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ይማጠናሉ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
“እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥
እግዚአብሔር በኮሬብ ካደረገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞዓብ ምድር ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደርገው ዘንድ ሙሴን ያዘዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።
“ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር ታደርጉት ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንዳስተምራችሁ ያዘዘው ትእዛዝና ሥርዐት፥ ፍርድም ይህ ነው።
አምላክህንም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ብትረሳ፥ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬውኑ ሰማይንና ምድርን አስመሰክርብሃለሁ።
የአዲስ ኪዳንም መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ ተረጨው ደሙ ደርሳችኋል።