2 ነገሥት 19:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጆቻቸው ዝለዋል፤ ደንግጠውም አፍረዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚኖሩባቸውም ሰዎች ኀይላቸው ተሟጥጦ ዐልቋል፤ ደንግጠውም የኀፍረት ማቅ ለብሰዋል፤ ሜዳ ላይ እንደ በቀለ ተክል፣ ገና እንዳልጠነከረ የቡቃያ ሥር፣ በቤት ጣራ ላይ በቅሎ፣ ገና ሳያድግ እንደ ጠወለገ ሣርም ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኃይላቸው ተዳክሞ፥ ተስፋ በመቁረጥ እንዳያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደ ተመቱ፥ የመስክ አትክልቶች፥ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፥ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኀይላቸው ተዳክሞ፥ ተስፋ በመቊረጥ እንዳያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደ ተመቱ፥ የመስክ አትክልቶች፥ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፥ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፤ ደንግጠውም ታውከዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል። |
ሽማግሎች ይደነግጣሉ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ይይዛቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም ይገዳደላሉ፤ ይደነቃሉ፤ ፊታቸውም እንደ እሳት ይንበለበላል።
ነገር ግን እናንተን የሚወጉትን የከለዳውያንን ጭፍራ ሁሉ ብትመቱ፤ ከእነርሱም ጥቂት ተወግተው ያልሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያንዳንዱ በስፍራው ይነሣሉ፤ ይህቺንም ሀገር በእሳት ያቃጥላሉ።”
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
እግዚአሔርም ሙሴን፥ “በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አትችልምን? አሁን ቃሌ ይፈጸም ወይም አይፈጸም እንደ ሆነ እነሆ፥ አንተ ታያለህ” አለው።
ነገር ግን እናንተ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እኛ እናጠፋቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጊዜአቸው አልፎባቸዋል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው” ብለው ተናገሩአቸው።