ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለንጉሡም ከኪራም አገልጋዮች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር፥ የዝሆንም ጥርስና ዝንጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለንጉሡም ከኪራም ባርያዎች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር የዝሆንም ጥርስ ዝንጀሮና ዝጉርጉር ወፍም ይዘው ይመጡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞንም በኪራም አገልጋዮች አማካይነት ወደ ተርሴስ የሚጓዙ መርከቦች ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመቱ ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለንጉሡም ከኪራም ባሪያዎች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር የዝሆንም ጥርስ ዝንጀሮና ዝንጕርጕር ወፍም ይዘው ይመጡ ነበር። |
ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።
ኢዮሣፍጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተርሴስ መርከብን ሠራ፤ ነገር ግን መርከቢቱ በጋሴዎንጋቤር ተሰብራለችና አልሄደችም።
ኪራምም መርከቦችንና የባሕርን ነገር የሚያውቁትን መርከበኞች በአገልጋዮቹ እጅ ላከለት፤ እነርሱም ከሰሎሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ሴፌር መጡ፤ ከዚያም አራት መቶ አምሳ መክሊት ወርቅ ወስደው ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎሞን አመጡ።
ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ሁሉ የወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር በተባለውም ቤቱ የሚገለገልበት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ ነበረ፤ በሰሎሞንም ዘመን ብር ከቶ አይቈጠርም ነበር።
የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር፥ ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው።
“ከኀይልሽ ሁሉ ብዛት የተነሣ የተርሴስ ሰዎች ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ገበያሽን ብር፥ ወርቅና ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስም አደረጉ።
የሮድያን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደስያት ሰዎችም የዝኆን ጥርስ ይነግዱልሽ ነበር፤ ከዚያም የመጡ ሰዎች ዋጋሽን ይሰጡሽ ነበር።
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።