Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሰሎሞንም በኪራም አገልጋዮች አማካይነት ወደ ተርሴስ የሚጓዙ መርከቦች ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመቱ ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ንጉሡ በኪራም ሰዎች የሚነዱ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች እየያዙ ይመለሱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ለንጉሡም ከኪራም ባርያዎች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር የዝሆንም ጥርስ ዝንጀሮና ዝጉርጉር ወፍም ይዘው ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ወደ ተር​ሴስ የሚ​ሄዱ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በሦ​ስት በሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ ጊዜ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ወር​ቅና ብር፥ የዝ​ሆ​ንም ጥር​ስና ዝን​ጀሮ ይዘው ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለንጉሡም ከኪራም ባሪያዎች ጋር ወደ ተርሴስ የሚሄዱ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር የዝሆንም ጥርስ ዝንጀሮና ዝንጕርጕር ወፍም ይዘው ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 9:21
11 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዐይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።


ንጉሥ ኪራም በሠለጠኑ መርከበኞች የሚነዱና በራሱ መኰንኖች የሚመሩ መርከቦችን ለሰሎሞን ልኮለት ነበር፤ እነርሱም ከሰሎሞን መኰንኖች ጋር በመሆን ወደ ኦፊር ምድር መጡ፤ ከዚያም ከዐሥራ አምስት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ ለሰሎሞን ይዘውለት መጡ።


ንጉሥ ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎችና “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ብር ከመብዛቱ የተነሣ ዋጋ እንዳለው ሆኖ አይቈጠርም ነበር።


“ሰጎን ክንፎችዋን በፍጥነት ትዘረጋለች፤ ነገር ግን እንደ ሸመላ አትበርም።


የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።


ምስሎቻቸው ከተርሴስ በመጣ ጥሬ ብርና ከኡፋዝ በተገኘ ወርቅ ተለብጠዋል፤ በብልኀተኞችም ሥራ አጊጠዋል፤ ጥበበኞች ሸማኔዎች በሠሩአቸውም የወይን ጠጅና ሐምራዊ ልብስ ተሸፍነዋል።


“ከብልጽግናሽ ብዛት የተነሣ ከተርሴስ ጋር ንግድ በመለዋወጥ በአንቺ ዕቃዎች ለውጥ ከእርስዋ ብር፥ ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስ ታገኚ ነበር።


ከሮድ አገር ሰዎች ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ በባሕር ዳር የሚገኙ አገሮች ሕዝቦች ሸቀጥሽን ወስደው በምትኩ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ያመጡልሽ ነበር።


ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos