1 ነገሥት 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አምላኬ እግዚአብሔር በዙሪያዬ ካሉት ዕረፍት ሰጥቶኛል፤ ክፉም ነገር የሚያደርግ ጠላት የለብኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን አምላኬ እግዚአብሔር በዙሪያዬ ሁሉ ሰላም ሰጥቶኛል፤ ጠላትም የለብኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን ጌታ እግዚአብሔር በሀገሬ ድንበር ዙሪያ ሁሉ ሰላም ሰጥቶኛል፤ ምንም ዓይነት አደጋ የሚጥል ጠላት የለብኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን አምላኬ እግዚአብሔር በሀገሬ ድንበር ዙሪያ ሁሉ ሰላም ሰጥቶኛል፤ ምንም ዐይነት አደጋ የሚጥል ጠላት የለብኝም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም አምላኬ እግዚአብሔር በዙሪያዬ ካሉት ዕረፍት ሰጥቶኛል፤ ጠላትም ክፉም ነገር የለብኝም። |
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ የእስራኤል ጠላት ነበረ። አዴርም ያደረጋት ክፋት ይህች ናት፤ እስራኤልን አስጨነቀ በኤዶምያስም ነገሠ።
ከወንዙ ወዲህ ባሉት ነገሥታት ሁሉ፥ ከወንዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙሪያውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖለት ነበር።
የሰሎሞንና የኪራም አናጢዎች፥ ጌባላውያንም ወቀሩአቸው፤ ለመሠረትም አኖሩአቸው፤ ቤቱንም ለመሥራት እንጨቱንና ድንጋዮቹን ሦስት ዓመት አዘጋጁ።
እነሆ፥ ልጅ ይወለድልሃል፤ የዕረፍት ሰውም ይሆናል፤ በዙሪያውም ካሉ ከጠላቶቹ ሁሉ አሳርፈዋለሁ፤ ስሙ ሰሎሞን ይባላልና፥ በዘመኑም ሰላምንና ጸጥታን ለእስራኤል እሰጣለሁ።
በኢየሩሳሌምም እጅግ ኀያላን ነገሥታት ነበሩ፤ በወንዝም ማዶ ያለውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና እጅ መንሻንም ይቀበሉ ነበር።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።
አሴያዶት መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም፥ ጋዛም መንደሮችዋና መሰማሪያዎችዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕርም ወሰኑ ነው።