Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 18:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም እስከ ጋዛና እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ፥ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ምሽጉ ከተማ ድረስ አጠፋ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እስከ ጋዛና እስከ ግዛቷ ዳርቻ በመዝለቅ ፍልስጥኤማውያንን ከመጠበቂያ ማማ እስከ ተመሸገችው ከተማ ድረስ ድል አደረጋቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ መንደር እስከ ታላቅ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት ጭምር እነርሱ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ ወረረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ መንደር እስከ ታላቅ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት ጭምር እነርሱ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ ወረረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ፍልስጥኤማውያንንም እስከ ጋዛና እስከ ዳርቻዋ ድረስ፥ ከዘበኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ምሽጉ ከተማ ድረስ መታ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 18:8
9 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያዬ ካሉት ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ክፉም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ጠላት የለ​ብ​ኝም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በአ​ም​ላ​ካ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ቅን ያል​ሆ​ነን ነገር በስ​ውር አደ​ረጉ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከዘ​በ​ኞች ግንብ ጀምሮ እስከ ተመ​ሸ​ገች ከተማ ድረስ በከ​ፍ​ታ​ዎች ላይ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን ሠሩ።


በስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ እነ​ዚ​ህም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን መጥ​ተው ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና በዚያ የተ​ገ​ኙ​ትን ምዑ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ሪያ ነበ​ርና በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


በም​ድረ በዳ​ውም ግን​ቦ​ችን ሠራ፤ ብዙ ጕድ​ጓ​ድም ማሰ፤ በቆ​ላ​ውና በደ​ጋው ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​ትና፤ ደግ​ሞም እርሻ ይወ​ድድ ነበ​ርና በተ​ራ​ራ​ማ​ውና በፍ​ሬ​ያ​ማው ስፍራ አራ​ሾ​ችና የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞች ነበ​ሩት።


ደግ​ሞም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን በቆ​ላ​ውና በደ​ቡብ በኩል ባሉት በይ​ሁዳ ከተ​ሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤት​ሳ​ሚ​ስ​ንና ኤሎ​ንን፥ ጋቤ​ሮ​ት​ንም፥ ሠካ​ዕ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ ቴም​ና​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም፥ ጋማ​ዚ​እ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወስ​ደው በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበር።


ፍል​ስ​ጥ​ኤም ሆይ፥ ከእ​ባቡ ዘር እፉ​ኝት ይወ​ጣ​ልና፥ ፍሬ​ውም የሚ​በ​ር​ርና እሳት የሚ​መ​ስል እባብ ይሆ​ና​ልና፥ የኀ​ይ​ላ​ችሁ ቀን​በር ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ሁላ​ች​ሁም ደስ አይ​በ​ላ​ችሁ።


አጥር አጠ​ርሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ቈፈ​ርሁ፤ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንም ለቅሜ አወ​ጣሁ፤ ምርጥ የሆ​ነ​ው​ንም ወይን ተከ​ልሁ፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግ​ሞም የመ​ጥ​መ​ቂያ ጕድ​ጓድ ማስ​ሁ​ለት፤ ወይ​ን​ንም ያፈራ ዘንድ ጠበ​ቅ​ሁት፤ ዳሩ ግን እሾ​ህን አፈራ።


እስከ ጋዛም ድረስ በአ​ሴ​ሮት ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን ኤዋ​ው​ያ​ን​ንና ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ የወጡ ቀጰ​ዶ​ቃ​ው​ያ​ንን አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ተቀ​መጡ።


አሴ​ያ​ዶት መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም፥ ጋዛም መን​ደ​ሮ​ች​ዋና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ፥ ታላቁ ባሕ​ርም ወሰኑ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos