Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እጅግ ኀያ​ላን ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ በወ​ን​ዝም ማዶ ያለ​ውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብ​ር​ንና እጅ መን​ሻ​ንም ይቀ​በሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ ማዶ ያለውን አገር ሁሉ የገዙ፣ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻም ይቀበሉ የነበሩ ኀያላን ነገሥታት ነበሯት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በኢየሩሳሌምም እጅግ ኃያላን ነገሥታት ነበሩ፥ በወንዝም ማዶ ያለውን አገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና ቀረጥን መጥንንም ይቀበሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህም ሁሉ ሆኖ፥ ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ በስተ ምዕራብ ያሉትን አገሮች ሁሉ በማስገበር ቀረጥና ግብር የሚያስከፍሉ ኀያላን ነገሥታት ነግሠውባት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በኢየሩሳሌምም እጅግ ኃያላን ነገሥታት ነበሩ፤ በወንዝም ማዶ ያለውን አገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና ቀረጥን መጥንንም ይቀበሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 4:20
23 Referencias Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


ዐስ​በው ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ። በአ​ር​ያ​ምም ዐመ​ፃን ተና​ገሩ።


ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


ደግ​ሞም በካ​ህ​ና​ቱና በሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ በመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ በበ​ረ​ኞ​ቹም፥ በና​ታ​ኒ​ምም በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ሠሩ አገ​ል​ጋ​ዮች ላይ ግብ​ርና ቀረጥ እን​ዳ​ይ​ጣል፥ የም​ት​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም አገ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ኖር ብለን እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለን።


ይህ​ችም ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ሰላም እን​ደ​ማ​ይ​ኖ​ርህ ለን​ጉሡ እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ለን።”


አሁ​ንም ይህች ከተማ የተ​ሠ​ራች እንደ ሆነ፥ ቅጥ​ር​ዋም የታ​ደሰ እንደ ሆነ፥ ግብ​ርና ቀረጥ መጥ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መን​ግ​ሥ​ትን ይጐ​ዳል።


ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ እጅ መን​ሻና የብር ግብር ያመጡ ነበር፤ ዐረ​ባ​ው​ያ​ንም ደግሞ ከመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በጎ​ች​ንና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየ​ሎ​ችን ያመ​ጡ​ለት ነበር።


ነጋ​ድ​ራ​ሶ​ችና ነጋ​ዴ​ዎች ከሚ​ያ​መ​ጡት ሌላ የዓ​ረብ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ የም​ድ​ሩም ሹሞች ወደ ንጉሡ ሰሎ​ሞን ወር​ቅና ብር ያመጡ ነበር


የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት እንደ ተሸ​ነፉ ባዩ ጊዜ ከዳ​ዊት ጋር ታረቁ፤ ተገ​ዙ​ለ​ትም፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዚያ ወዲያ የአ​ሞ​ንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ።


በዚ​ያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።


ከወ​ንዙ ወዲህ ባሉት ነገ​ሥ​ታት ሁሉ፥ ከወ​ን​ዙም ወዲህ ባለው ሀገር ሁሉ ላይ ከቲ​ላሳ ጀምሮ እስከ ጋዛ ድረስ ነግሦ ነበር፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ባለው በሁሉ ወገን ሰላም ሆኖ​ለት ነበር።


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


እኔም አዝ​ዣ​ለሁ፤ ተመ​ረ​መ​ረም፤ ይህ​ችም ከተማ ከጥ​ንት ጀምራ በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ዐመ​ፀኛ እንደ ነበ​ረች፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዐመ​ፅና ሽፍ​ት​ነት እንደ ተደ​ረገ ተገኘ።


አሁ​ንም እነ​ዚህ ሰዎች ሥራ​ውን እን​ዲ​ተዉ፥ ይህ​ችም ከተማ እን​ዳ​ት​ሠራ ትእ​ዛዝ ስጡ።


አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ።


አሁ​ንም አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያዬ ካሉት ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ክፉም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ጠላት የለ​ብ​ኝም።


ከእ​ር​ስ​ዋም የጸ​ናች በትር ወጣች፤ ለገ​ዥ​ዎ​ችም በትር ሆነች፤ በዛ​ፎ​ችም መካ​ከል ቁመቷ ረዘመ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም ርዝ​መቷ ታየ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios