ከከፉ ነገር ሁሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም፥ የአባቶች የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”
1 ነገሥት 1:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም እንዲህ ብሎ ማለ፥ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳናት ሕያው እግዚአብሔርን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፦ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ባዳነኝ በሕያው ጌታ ቃል እገባለሁ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ እንዲህ አላት፥ “ከደረሰብኝ መከራ ሁሉ በታደገኝ በሕያው እግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሻለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን! |
ከከፉ ነገር ሁሉ የአዳነኝ መልአክ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም፥ የአባቶች የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”
ዳዊትም ለቤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፥ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነ ሕያው እግዚአብሔርን!
በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ፥ ይፈልግህ ዘንድ ያልላከበት ሕዝብ ወይም መንግሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አንተን እንዳላገኙ መንግሥቱንና ሕዝቡን አምሎአቸው ነበር።
አሁንም ያጸናኝ፥ በአባቴም በዳዊት ዙፋን ላይ ያስቀመጠኝ፥ እንደ ተናገረውም ቤትን የሠራልኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ዛሬ አዶንያስ ፈጽሞ ይገደላል።
ኤልሳዕም፥ “በፊቱ የቆምሁት ሕያው እግዚአብሔርን! አልቀበልም” አለ። ይቀበለውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።
የኤልሳዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፤ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተኋላው እሮጣለሁ፤ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ” አለ።
ጌዴዎንም፥ “የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ነበሩ፤ አድናችኋቸው ቢሆን ኖሮ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ አልገድላችሁም ነበር” አለ።
እስራኤልን የሚያድን ሕያው እግዚአብሔርን! ኀጢኣቱ በልጄ በዮናታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞታል” አለ። ከሕዝቡም ሁሉ አንድ የመለሰለት ሰው አልነበረም።
ሕዝቡም ሳኦልን፥ “በውኑ በእስራኤል ዘንድ ታላቅ መድኀኒት ያደረገ ዮናታን ዛሬ ይሞታልን? ይህ አይሁን፤ ዛሬ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር አድርጎአልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራሱ ጠጕር አንዲት በምድር ላይ አትወድቅም” አሉት። ሕዝቡም ያን ጊዜ ስለ ዮናታን ጸለዩ፤ እርሱም አልተገደለም።
እነሆም፦ ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ ብዬ ብላቴናውን እልካለሁ፤ ብላቴናውንም፦ እነሆ፥ ፍላጻው ከአንተ ወደዚህ ነው፤ ይዘኸው ወደ እኔ ና ያልሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለብህም።