1 ነገሥት 1:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 በእውነት፦ ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በእኔም ምትክ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር የማልሁልሽን ዛሬ በእውነት እፈጽማለሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 በእውነት ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል ብዬ በእስራኤል አምላክ በጌታ እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ” ብሎ ማለ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ልጅሽ ሰሎሞን በእኔ እግር ተተክቶ እንደሚነግሥ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ከዚህ በፊት የገባሁልሽን ቃል በዛሬው ዕለት የምፈጽም መሆኔን አረጋግጥልሻለሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 በእውነት ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በእኔም ፋንታ በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል፤’ ብዬ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር እንደ ማልሁልሽ፥ እንዲሁ ዛሬ በእውነት አደርጋለሁ፤” ብሎ ማለ። Ver Capítulo |