መዝሙር 9:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትን አድርግልኝ! ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት! ከሞትም አድነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤ አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የሚያደርገኝ፤ |
እግዚአብሔርም ቃየልን “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤ ቃየልም “የት እንዳለ አላውቅም፤ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” ብሎ መለሰ።
እኔ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የምለው ይህ ነው ‘ናቡቴን መግደልህ አንሶህ ሀብቱንም ልትወርስበት ነውን?’ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ እንዲሁም የአንተን ደም ይልሱታል!’ ”
‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቅን አገልግሎት በመዘንጋት ዘካርያስን ገደለ፤ ዘካርያስም ሊሞት ሲያጣጥር ሳለ “እግዚአብሔር ይህን ግፍ ተመልክቶ ይቅጣህ” አለ።
“ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ።
ሕዝብዋ ምግብ ማግኘት ፈልገው ይቃትታሉ፤ በሕይወት ለመኖር ሲሉ ሀብታቸውን ሁሉ በምግብ ይለውጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ “እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከተን! ውርደታችንን ሁሉ እይልን!” እያሉ ይጮኻሉ።
አደፍዋ በቀሚስዋ ላይ ይታያል፤ ለወደፊት ምን እንደሚደርስባት አላሰበችም፤ አወዳደቅዋ የሚያሰቅቅ ነው፤ የሚያጽናናት ከቶ የለም፤ ጠላቶችዋ ድል ስላደረግዋት፥ መከራዋን እንዲመለከትላት ወደ እግዚአብሔር ጸለየች።
አይሁድ የመንጻት ሥርዓት ስለ ነበራቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱ ጋን ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ውሃ ለመያዝ ይችል ነበር።