መዝሙር 49:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሳቤን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፤ የምሳሌዎችንም ትርጒም በገና በመደርደር እገልጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤ እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አስተንትኖ ማስተዋልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥ |
ስለዚህም እኔ ከእርሱ ጋር ቃል ለቃል በግልጥ እነጋገራለሁ እንጂ ስውር በሆነ አነጋገር አልናገረውም፤ የእኔን የእግዚአብሔርን መልክ ያያል፤ ታዲያ፥ እናንተ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ እንዴት ደፈራችሁ?”
በለዓምም እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ “የሞአብ ንጉሥ ባላቅ የምሥራቅ ተራራዎች ከሚገኙበት ከሶርያ ጠርቶ አመጣኝ። እርሱም ‘ና፤ የእስራኤልን ሕዝብ አውግዝልኝ፤ እንዲጠፉም ርገምልኝ’ አለኝ።
ይህም የሆነበት ምክንያት በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው፦ “ንግግሬን በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውን እናገራለሁ።”