Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 49:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ክፉ ቀን ሲመጣና ክፉዎች አታላዮች ሲከቡኝ ለምን እፈራለሁ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጆሮዬን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እንደ ሕጉ መሥ​ዋ​ዕ​ትን የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ ጻድ​ቃ​ኑን ሰብ​ስ​ቡ​ለት።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 49:5
19 Referencias Cruzadas  

‘ጳውሎስ ሆይ! አትፍራ! በሮም ንጉሠ ነገሥት ፊት መቆም ይገባሃል! እነሆ፥ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሁሉ እግዚአብሔር ለአንተ ብሎ ከሞት ያድናቸዋል’ ብሎ ነግሮኛል።


ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ድፍረታችሁ ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳኛችሁ ምልክት ነው።


ይህ ዘመን ክፉ ስለ ሆነ በማናቸውም አጋጣሚ ጊዜ ተጠቀሙ።


ስለዚህ ዘመኑ ክፉ ስለ ሆነ አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል።


ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”


መከራ በሚደርስብህ ጊዜ መጽናት የማትችል ከሆንክ ምንም ብርታት የለህም ማለት ነው።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


በደሌ በራሴ ላይ ተጭኖአል፤ እርሱም ለመሸከም ከምችለው በላይ ነው።


በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።


ክፉ ሰዎች እንደ ውሻ ስብስብ ከበቡኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ።


ከእግዚአብሔር ርቄ በባዕድ አገር እንድገደል አታድርግ፤ ይህን ያኽል ታላቅ የሆነ የእስራኤል ንጉሥ እንደ ቁንጫ የምቈጠረውን እኔን ስለምን ያሳድዳል? እንደ በረሓ ቆቅ የሚያድነኝስ ስለምንድን ነው?”


ፈረሰኛው ሰው ወደኋላው ይወድቅ ዘንድ፥ ዳን እንደ ነዳፊ እባብ ሆኖ፥ በመተላለፊያው መንገድ ላይ የፈረሱን ሰኰና ይነክሳል።


በለዓምም እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፦ “የሞአብ ንጉሥ ባላቅ የምሥራቅ ተራራዎች ከሚገኙበት ከሶርያ ጠርቶ አመጣኝ። እርሱም ‘ና፤ የእስራኤልን ሕዝብ አውግዝልኝ፤ እንዲጠፉም ርገምልኝ’ አለኝ።


ንግግሬን በምሳሌ እጀምራለሁ፤ ከጥንት ጀምሮ የተሰወረውን ምሥጢር እገልጣለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios