መዝሙር 49:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ! በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ምድርንም ጠራት፤ ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
እስቲ ልጠይቅ፤ ታዲያ፥ ቃሉን አልሰሙም ማለት ነውን? በቅዱስ መጽሐፍ፥ “ድምፃቸው በዓለም ሁሉ ተሰማ፤ ቃላቸውም እስከ ምድር ዳርቻ ደረሰ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ በእርግጥ ሰምተዋል።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይም እሰጠዋለሁ፤ ከተቀባዩ በቀር ይህን ሌላ ማንም አያውቀውም።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’