መዝሙር 144:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ጠባቂዬና መከታዬ ነው፤ መጠለያዬና አዳኜ ነው፤ በእርሱ ተማምኜ በሰላም እኖራለሁ፤ እርሱ አሕዛብን ከእግሬ በታች አድርጎ ያስገዛልኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ ምሽጌና ታዳጊዬ፣ የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፥ ረዳቴና መታመኛዬም፥ ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየቀኑ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም ለዘለዓለም ዓለም ምስጋና አቀርባለሁ። |
እግዚአብሔር ሆይ! የምትጠብቀኝና ብርታትን የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ አምባዬ ነህ፤ ሕዝቦች ከምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “የቀድሞ አባቶቻችን ከሐሰተኞች አማልክት በቀር ምንም አልነበራቸውም፤ ጣዖቶቻቸው ሁሉ የማይጠቅሙ ከንቱዎች ነበሩ፤