መዝሙር 142:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አመሰግንህ ዘንድ ከእስራቴ አውጣኝ፤ ለእኔ ያደረግኸውን ያንተን የቸርነት ሥራ በሚያዩበት ጊዜ ሕዝብህ በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከእስር አውጣት፤ ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ ሰውነቴ አልቃለች፤ ፊትህንም ከእኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን። |
ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።
ደግሞም እነዚያን በትዕግሥት የጸኑትን “የተባረኩ ናቸው” እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንዴት እንደ ታገሠ ሰምታችኋል። ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን መልካም ነገር አይታችኋል፤ በዚህም ጌታ መሐሪና ርኅሩኅ መሆኑን ተመልክታችኋል።