Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 142:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አቤቱ፥ ፈጥ​ነህ ስማኝ፥ ሰው​ነቴ አል​ቃ​ለች፤ ፊት​ህ​ንም ከእኔ አት​መ​ልስ፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም እን​ደ​ሚ​ወ​ርዱ አል​ሁን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከእስር አውጣት፤ ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣ ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አመሰግንህ ዘንድ ከእስራቴ አውጣኝ፤ ለእኔ ያደረግኸውን ያንተን የቸርነት ሥራ በሚያዩበት ጊዜ ሕዝብህ በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 142:7
20 Referencias Cruzadas  

ደምን ለማ​ፍ​ሰስ እግ​ራ​ቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋ​ትና ጕስ​ቍ​ልና በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አለ፥ የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አላ​ወ​ቁ​አ​ት​ምና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በዐ​ይ​ና​ቸው ፊት የለም።


አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን ስማ፥ በእ​ው​ነ​ትህ ልመ​ና​ዬን አድ​ምጥ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም መል​ስ​ልኝ።


አፋ​ቸ​ውም ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ፥ ከባ​ዕድ ልጆች እጅ አድ​ነኝ፥ አስ​ጥ​ለ​ኝም።


አቤቱ፥ በአ​ዲስ ምስ​ጋና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዐሥር አው​ታር ባለው በገ​ናም እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ስ​ጋና ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በመ​ሰ​ንቆ ዘምሩ፤


አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ፥ በም​ት​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ አጸ​ና​ሃ​ለሁ። ዐይ​ኖ​ቼን በአ​ንተ ላይ አጸ​ና​ለሁ።


ጋሻና ጦር ያዝ፥ እኔ​ንም ለመ​ር​ዳት ተነሥ።


ምስ​ጋ​ና​ውን ሁሉ እና​ገር ዘንድ፤ በጽ​ዮን ልጅ በደ​ጆ​ችዋ፥ በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ናል።


ጠላ​ቶቼ ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለሱ ጊዜ፥ ይታ​መሙ፥ ከፊ​ት​ህም ይጥፉ።


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።


እነሆ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፤ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos