ዘኍል 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም ሌሊቱን ሁሉ በመጨነቅ ሲጮኹ አደሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ሌሊት ማኅበረ ሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸና አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ጮኹ፤ በዚያም ሌሊት ሕዝቡ አለቀሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን አንስተው ጮኹ፤ ሕዝቡም ሌሊቱን ሁሉ አለቀሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩም ሁሉ ድምፃቸውን አንሥተው ጮኹ፤ ሕዝቡም በዚያ ሌሊት አለቀሱ። |
የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቅርብ በሆነው በፍልስጥኤም የባሕር ጠረፍ በኩል ባለው መንገድ አልመራቸውም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ከፊት ለፊታቸው ጦርነት እንደሚጠብቃቸው በሚያዩበት ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ነው።
በዚያም ከኔፊሊም ወገን የሆኑትን የዐናቅን ዘሮች አይተናል፤ እኛ በእነርሱ ፊት ልክ እንደ ፌንጣ ያኽል ሆነን ነበር የታየነው፤ እነርሱም እንደዚያው አድርገው ሳይመለከቱን አይቀሩም” አሉ።
እግዚአብሔር፥ ‘ሂዱ፤ የሰጠኋችሁንም የተስፋ ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁም ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፃችሁ እንጂ አልተማመናችሁበትም፤ ለቃሉም አልታዘዛችሁም።
ከእኔ ጋር ሄደው የነበሩ ሰዎች ግን የሕዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ እኔ ግን ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ታዛዥ ሆኛለሁ፤