አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤
ነህምያ 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን ንግግሬን በመቀጠል እንዲህ አልኳቸው፤ “ያደረጋችኹት ነገር ትክክል አይደለም! እግዚአብሔርን መፍራትና ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤ ይህን አድርጋችሁ ቢሆን ኖሮ፥ አሕዛብ ጠላቶቻችን ባልተዘባበቱብንም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በመቀጠል እንዲህ አልሁ፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ትክክል አይደለም፤ የጠላቶቻችንን የአሕዛብን ስድብ ለማስወገድ የአምላካችንን መንገድ በፍርሀት መከተል አይገባችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አልኳቸው፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት መሄድ አይገባችሁምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም አልሁ፥ “የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፤ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም አልሁ፦ የምታደርጉት ነገር መልካም አይደለም፥ ጠላቶቻችን አሕዛብ እንዳይሰድቡን አምላካችንን በመፍራት ትሄዱ ዘንድ አይገባችሁምን? |
አብርሃምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘እዚህ ቦታ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የለም’ ብዬ በማሰብ ‘ሚስቴን ለመውሰድ በመፈለግ ይገድሉኛል’ ብዬ ስለ ሰጋሁ ነው፤
እኔም እንዲህ ስል ጸለይሁ፤ “አምላክ ሆይ! እንዴት እንደሚሳለቁብን ተመልከት፤ ይህም ስድባቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው፤ ያላቸውን ሀብት ሁሉ ተገፈው በባዕድ አገር ስደተኞች ይሁኑ፤
ሕዝቡ ከእኔ ገንዘብም ሆነ እህል እንዲበደሩ ፈቅጄላቸዋለሁ፤ የሥራ ባልደረቦቼና የእኔ አገልጋዮች የሆኑት ሁሉ እንዲሁ ያደርጉ ዘንድ ፈቅጃለሁ፤ እንግዲህስ ‘የተበደራችሁትን ዕዳ ክፈሉን’ ብለን መጠየቅ ይቅርብን፤
ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።
እነዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ እርሱ ከሰጣቸው ምድር ወጥተዋል” ብለው የተበታተኑባቸው አገሮች ሕዝቦች ስለሚናገሩ ሕዝቤ ቅዱስ ስሜን አሰድበዋል።
በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።
ስለዚህ በዕድሜአቸው ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፥ ልጆችን እንዲወልዱ፥ ቤታቸውንም በሚገባ እንዲያስተዳድሩ እመክራለሁ፤ በዚህ ዐይነት ጠላት ለስም ማጥፋት ምክንያት ያጣል።
ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።