Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 90:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አንተን የሚፈሩ ሰዎች ቊጣህን የሚረዱትን ያኽል፥ የአንተን የቊጣ ኀይል የሚያውቅ ማነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል? የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በመ​ን​ገ​ድህ ሁሉ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ቱን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 90:11
12 Referencias Cruzadas  

በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ።


በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።


በእናንተ ላይ በቊጣ ተመልሼ ካለፈው ሰባት እጥፍ በበረታ ሁኔታ እቀጣችኋለሁ።


ታላቁ የቊጣ ቀን መጥቶአል፤ ማን ሊቋቋመው ይችላል?” አሉአቸው።


ጌታን መፍራት ምን መሆኑን ስለምናውቅ ሰዎችን እናስረዳለን፤ እኛ ምን መሆናችንንም እግዚአብሔር ያውቃል፤ እናንተም በልቡናችሁ ምን መሆናችንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።


እግዚአብሔር በአንተና በልጆችህ ላይ አስፈሪ፥ ለብዙ ጊዜ የሚቈይ መቅሠፍትና ከባድ የማይድን በሽታ ያመጣብሃል።


“እኔን በመቃወም ከቀጠላችሁና እኔን የማትሰሙኝ ከሆነ፥ እንደ ኃጢአታችሁ ብዛት ሰባት ጊዜ እጥፍ የሆነ መቅሠፍት አመጣባችኋለሁ።


“ይህም ሁሉ ከደረሰባችሁ በኋላ እንኳ የማትታዘዙኝ ከሆናችሁ፥ በእናንተ ላይ የማመጣውን ቅጣት ሰባት ጊዜ እጥፍ እንዲበዛ አደርገዋለሁ።


ነገር ግን ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ እነግራችኋለሁ፤ ይኸውም ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እግዚአብሔርን ነው፤ አዎ፥ እርሱን ብቻ ፍሩ እላችኋለሁ!


እግዚአብሔር ሆይ አንተ ግን በሁሉ ዘንድ የተፈራህ ነህ፤ አንተ ስትቈጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ አይኖርም፤


በእናንተ ላይ በቊጣ እነሣለሁ፤ በእናንተ ላይ የማመጣውንም ቅጣት ካለፈው ሰባት ጊዜ የበለጠ እንዲሆን አደርጋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios