Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 24:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የጥበበኞች ተጨማሪ አባባሎች፦ በዳኝነት ማዳላት ስሕተት ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እነዚህም ደግሞ የጠቢባን ምሳሌዎች ናቸው፦ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነዚህ ደግሞ የጠቢባን ቃሎች ናቸው። በፍርድ ላይ ማዳለት መልካም አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 24:23
18 Referencias Cruzadas  

ፍትሕ ማጓደል ወይም ማድላት ወይም ጉቦ መቀበል በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ የሌሉ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን በመፍራት ትክክለኛ ፍርድ ስጡ።”


ለእርሱ ታደሉለታላችሁን? ለእርሱስ ጥብቅና ትቆማላችሁን?


ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ ይህን ያስተውሉ፤ ዘለዓለማዊውን የእግዚአብሔርን የፍቅር ሥራ ይገንዘቡ።


በዚህ ዐይነት ስውር የሆኑ የምሳሌዎችን ምሥጢር ጠቢባን የሚያቀርቡአቸውን እንቆቅልሾች መረዳት ያስችላሉ።


ለበደለኛው ማዳላትና ንጹሕ ሰው ትክክለኛ ፍትሕ እንዳያገኝ ማድረግ ተገቢ አይደለም።


ጠቢባን ሰዎች የተናገሩትን ሳስተምርህ አድምጥ፤ ከእነርሱ የምታገኘውን ትምህርት አጥና፤


አድልዎ ማድረግ አይገባም፤ አንዳንድ ሰው ግን ቊራሽ እንጀራ ለማግኘት ብሎ ያደላል።


ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።


“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።


ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ እንጂ የሰውን ፊት አይታችሁ በማዳላት አትፍረዱ።”


በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’


ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህ አታድላ፤ አታታል፤ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ስለሚያሳውርና የተጣመመ ፍርድ ስለሚያሰጥ ጉቦ አትቀበል።


ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።


ለማንም ሳያዳላ ለያንዳንዱ እንደየሥራው የሚፈርደውን እግዚአብሔርን “አባታችን” ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ በዚህ ዓለም በእንግድነት መጻተኞች ሆናችሁ ስትኖሩ እርሱን በመፍራት ኑሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos