እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
ዮሐንስ 9:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳነጋገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ ሆነ አናውቅም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ እንኳ አናውቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደሆነ አናውቅም፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተነጋገረው እናውቃለን፤ ይህን ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እኛ እናውቃለን፥ ይህ ሰው ግን ከወዴት እንደ ሆነ አናውቅም” አሉት። |
እኔም በደኅና እስክመለስ ድረስ በእስር ቤት አስገብተው ደረቅ እንጀራና ውሃ ብቻ እየሰጡት እንዲቈይ ያደርጉ ዘንድ በእኔ ስም ንገራቸው” ሲል አዘዘው።
ኢዩም፦ ጓደኞቹ ወደሆኑት ወደ ጦር መኰንኖቹ በመጣ ጊዜ “ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ከአንተ ምን ይፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ” አላቸው።
በዚያን ጊዜ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህን ሁሉ ሥራ እንዳከናውን እግዚአብሔር እኔን የላከኝ መሆኑን የምታውቁትና እኔ ይህን ሁሉ ሥራ የማከናውነው በራሴ ፈቃድ እንዳልሆነ የምትገነዘቡት በዚህ ነው፤
እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”
ስለዚህ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከወዴትም እንደ መጣሁ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም፤ የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው፤ እናንተ ግን አታውቁትም።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ምንም እንኳ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ከየት እንደ መጣሁ፥ ወዴትም እንደምሄድ ስለማውቅ ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።
በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ።
በዚህ ምክንያት ዕውር የነበረውን ሰው እንደገና ጠርተው “አንተ እውነቱን በመናገር እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት።
እስከዚህ ድረስ ሕዝቡ ሁሉ የጳውሎስን ንግግር ያዳምጡ ነበር፤ ከዚህ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፦ “እንዲህ ዐይነቱ ሰው ከምድር ላይ ይወገድ! እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት መኖር አይገባውም!” እያሉ ጮኹ።
እስከ ዛሬ ድረስ የእግዚአብሔር ርዳታ አልተለየኝም፤ ስለዚህ ለትንሹም ለትልቁም እየመሰከርኩ እዚህ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ አስቀድመው እንዲህ ይሆናል ያሉትን ከመናገር በቀር ሌላ ምንም አልተናገርኩም።
“የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን ‘በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው?’ በማለት ተቃውመውት ነበር፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንኑ ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በተገለጠለት መልአክ አማካይነት ገዢና ነጻ አውጪ አድርጎ ወደ እነርሱ ላከው።
አሁን ግን በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ሁሉን ነገር ወራሽ ባደረገው በልጁ አማካይነት ለእኛ ተናገረን፤ ዓለምንም ሁሉ የፈጠረው በእርሱ ነው።