ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
ኤርምያስ 51:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድራቸው በእኔ በእስራኤል ቅዱስ ዘንድ በበደል የተሞላች ብትሆንም እንኳ እኔ የሠራዊት ጌታ አምላካቸው እስራኤልንና ይሁዳን አልረሳኋቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ፊት፣ በበደል የተሞላች ብትሆንም፣ እስራኤልንና ይሁዳን አምላካቸው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አልጣላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ ዘንድ አልተተዉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል የተሞላች ብትሆንም፥ እስራኤል መበለት አልሆነችም፤ ይሁዳም ከአምላኩ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልራቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላኩ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጣለም። |
ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
እኛ ባርያዎች ነበርን፤ አንተ ግን ባርያዎች ሆነን እንድንቀር አልተውከንም፤ አንተ የፋርስ ነገሥታት እንዲራሩልንና በሕይወት ነጻ ወጥተን ቀደም ሲል ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደስህን እንደገና መልሰን እንድንሠራ፥ እዚህም በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሰላም እንድንኖር ፈቀድክልን።
ሕዝቡ “የተቀደሱና እግዚአብሔር የታደጋቸው ወገኖች” ተብለው ይጠራሉ፤ አንቺም ኢየሩሳሌም “የተፈለገችና ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪአለሽ።
እግዚአብሔር ሆይ! ይሁዳን ፈጽመህ ልትጥላት ነውን? የጽዮንንስ ሕዝብ እንደ ጠላህ መቅረትህ ነውን? ለመፈወስ እስከማንችል ድረስ፥ ይህን ያኽል እንድንጐዳ ማድረግህስ ስለምንድን ነው? ሰላም እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፥ ነገር ግን ምንም መልካም ነገር አልገጠመንም፤ ፈውስ እናገኛለን ብለን ተስፋ አደረግን፤ ነገር ግን ሽብር እየበዛ ሄደ።
ለምን ግራ እንደ ተጋባ ሰውና ሌላውን መርዳት እንደማይችል ኀይለኛ ወታደር ትሆናለህ? እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን በመካከላችን ነህ፤ በስምህም እንጠራለን፤ እባክህ አትተወን።’ ”
እንደ በድን ሕይወት በሌላቸው ጣዖቶች ርስቴን ስላረከሱና በሐሰተኞች አማልክታቸው ስለ ሞሉአት ስለ ኃጢአታቸውና ስለ ክፋታቸው በእጥፍ እቀጣቸዋለሁ።”
ይህንንም የማደርገው ሕዝቡ እኔን ስለ ተዉና ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ይህን ስፍራ ስላረከሱ ነው፤ እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው ከይሁዳ ነገሥታት ጭምር ስለ ነዚህ አማልክት የሚያውቁት ነገር የለም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ንጹሖች ሰዎችን በመግደል ይህ ስፍራ በደም የተሞላ እንዲሆን አድርገውታል።
“እንግዲህ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ነቢያት የምለው ይህ ነው፦ ‘በምድሪቱ ሁሉ ላይ የክሕደትን መንፈስ ስላሠራጩ፥ መራራ ቅጠል እንዲበሉና መርዝ እንዲጠጡ አደርጋቸዋለሁ።’ ”
እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በሠሩት በደል ምክንያት ይጥላቸዋል ማለት የሚቻለው የሰማይ ስፋቱ ተለክቶ፥ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተመርምረው ለመታወቅ ቢችሉ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የያዕቆብ አምላክ ግን እንደ እነርሱ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንዲሆን እስራኤልን መርጦታል፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ታያለህን? እነዚህ የይሁዳ ሕዝቦች በዚህ ስፍራ ያየኸውን አጸያፊ ነገር ሁሉ በመሥራትና በአገሪቱም ላይ ዐመፅ ማስፋፋቱ አልበቃ ብሎአቸው ወደዚህ ወደ ቤተ መቅደስ እንኳ ሳይቀር በቀጥታ መጥተው ይህን ሁሉ በማድረግ እኔን እንደገና ማስቈጣት ይፈልጋሉ፤ እንዴት እንደሚሰድቡኝና እኔን ለማስቈጣት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተመልከት!
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ እጅግ የከፋ ኃጢአት በመሥራት በድለዋል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ከተማይቱንም በዐመፅ የተሞላች አድርገዋታል፤ ‘እግዚአብሔር አገራችንን ትቶአታል፤ እኛንም አይመለከተንም’ ይላሉ፤
የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤
በዚህች ምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ወቀሳ አለው፤ ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እርሱ የሚልህን ሁሉ ስማ፦ “በምድሪቱ ላይ ታማኝነትና ፍቅር እግዚአብሔርንም ማወቅ ጠፍቶአል።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
“በዚያን ጊዜ የይሁዳን ሕዝብ አለቆች በእሳት ማንደጃ ላይ ተከምሮ እንደሚነድ እንጨት፥ በእህል ነዶዎች መካከል እንደ ተቀጣጠለ ችቦ አደርጋቸዋለሁ፤ በአካባቢው ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያወድማሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ግን ምንም ሳይደርስባቸው በከተማይቱ ውስጥ ይኖራሉ።
በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንደ ጋሻ መከታ እሆንላቸዋለሁ፤ ከእነርሱ እጅግ ደካማ የተባለው እንኳ የዳዊትን ያኽል ብርቱ ይሆናል፤ የዳዊት ልጆች እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ወይም እንደ መላእክት ሆነው ሕዝቡን ይመራሉ።