እርሱም የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ “በእርግጥ የእርሱ ልብስ ነው! አንድ ክፉ አውሬ ገድሎታል፤ ልጄን ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆ በልቶታል!” አለ።
ዘፍጥረት 38:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳም ዕቃዎቹ የማን እንደ ሆኑ ዐውቆ “ከልጄ ከሴላ ጋር ስላላጋባኋት እርስዋ ከእኔ ይልቅ ትክክለኛ ሆና ተገኘች” አለ፤ ወደ እርስዋም ዳግመኛ አልገባም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከርሷ ጋራ አልተኛም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፥ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፥ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕማር እውነተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና” አለ። ትገደል ማለትንም ተወ፤ ደግሞም አላወቃትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም አወቀ፦ ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነትኛ ሆነች ልጄን ሴሎምን አልሰጠኍትምና አለ። ደግሞም አላወቃትም። |
እርሱም የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ “በእርግጥ የእርሱ ልብስ ነው! አንድ ክፉ አውሬ ገድሎታል፤ ልጄን ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆ በልቶታል!” አለ።
ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።
አዳም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “በእግዚአብሔር ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” ስትል “ቃየል” የሚል ስም አወጣችለት።
ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ በደረሰ ጊዜ፥ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁለት ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥር ቊባቶቹን ወደ ሌላ ወስዶ በዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፤ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሰጣቸው አዘዘ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አልፈጸመም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው በቤት ተወስነው እንደ መበለቶች በመሆን ኖሩ።
ዳዊትም ሕዝቡን ይቀሥፍ የነበረውን መልአክ አይቶ እግዚአብሔርን “በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ እኔም ራሴ ክፉ ነገርን አደረግሁ፤ ታዲያ ይህ ምስኪን ሕዝብ ምን በደለህ? ይህ መቅሠፍት በእርሱ ላይ ከሚወርድ ይልቅ በእኔና በቤተሰቤ ላይ ይሁን” ሲል ጠየቀ።
እነሆ አሁንም ውርደትሽን ተሸከሚ፤ የአንቺ ኃጢአት እጅግ የከፋ ከመሆኑ የተነሣ እኅቶችሽ ከአንቺ ጋር ሲነጻጸሩ ምንም በደል የሌለባቸው ንጹሖች መስለው ይታያሉ፤ አሁንም እኅቶችሽን በደል የሌለባቸው ንጹሖች እንዲመስሉ በማድረግሽ ኀፍረትን እንደ ልብስ ተከናንበሽ ተቀመጪ።”
ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?
እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
ከዚያም በኋላ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “አንተ እውነተኛ ሰው ነህ! እኔ ግን ስሕተተኛ ነኝ፤ ይህን የመሰለ በደል ስፈጽምብህ አንተ ለእኔ ቸርነት አድርገህልኛል!