Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 24:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከዚያም በኋላ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “አንተ እውነተኛ ሰው ነህ! እኔ ግን ስሕተተኛ ነኝ፤ ይህን የመሰለ በደል ስፈጽምብህ አንተ ለእኔ ቸርነት አድርገህልኛል!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንዲህም አለው፤ “ክፉ ሳደርግብህ፣ በጎ መልሰህልኛልና፣ አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዳዊት ይህን ተናግሮ ሲያበቃ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ሲል ጠየቀው፤ ሳኦል ጮኾም አለቀሰ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳ​ኦል መን​ገር በፈ​ጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦ​ልም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዳዊትን አለው፦ እኔ ክፉ በመለስሁልህ ፋንታ በጎ መልሰህልኛልና አንተ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ነህ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 24:17
8 Referencias Cruzadas  

ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ።


እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።


ይሁዳም ዕቃዎቹ የማን እንደ ሆኑ ዐውቆ “ከልጄ ከሴላ ጋር ስላላጋባኋት እርስዋ ከእኔ ይልቅ ትክክለኛ ሆና ተገኘች” አለ፤ ወደ እርስዋም ዳግመኛ አልገባም።


“ንጹሑን ሰው ለሞት አሳልፌ በመስጠቴ በድዬአለሁ።” እነርሱ ግን “ታዲያ፥ እኛ ምን ቸገረን! የራስህ ጉዳይ ነው!” አሉት።


ጽድቅህን እንደ ብርሃን የጉዳይህንም ትክክለኛነት እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል።


ንጉሡም ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንስ በድዬአለሁ፤ እግዚአብሔር እውነተኛ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን በደለኞች ነን።


ሳኦልም የዳዊትን ድምፅ ለይቶ ስላወቀ “ዳዊት ልጄ ሆይ! በእርግጥ ይህ ቃል የአንተ ነውን?” ሲል ጠየቀ። ዳዊትም “አዎ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ድምፄ ነው ሲል መለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios