ዮሐንስ 8:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እነርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊናቸው ወቅሶአቸው ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ኋለኞቹ ድረስ፥ አንዳንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታችን ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴትዮዪቱም በመካከል ቆማ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸዋና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። Ver Capítulo |