ዘፍጥረት 20:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ እንደ ገናም ልጅ ለመውለድ በቍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባርያዎቹንም ፈወሳቸው፥ እነርሱም ወለዱ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ወደ እግዚዘብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፥ ሚስቱንም፥ ሴቶች ልጆቹንም፥ በቤቱ ውስጥ ያሉ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈወሳቸው፤ እነርሱም ወለዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንምም ፈውሳቸው |
አሁን ግን ሴቲቱን ለባልዋ መልሰህ ስጥ፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ እንዳትሞት ይጸልይልሃል፤ እርስዋን መልሰህ ባትሰጥ ግን እንደምትሞት ዕወቅ፤ አንተ ብቻ ሳትሆን ሕዝብህም በሙሉ ታልቃላችሁ።”
ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”
ቅዱስ የእስራኤል አምላክና፥ ፈጣሪ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለ ልጆቼ ልትጠይቁኝና ወይም ስለ እጆቼ ሥራ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ልታዙኝ ትደፍራላችሁን?
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ክፉ ቃል በመናገራችን በድለናል፤ አሁንም እነዚህ ተናዳፊ እባቦች ከእኛ እንዲወገዱ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት፤ ሙሴም ለሕዝቡ ጸለየ።
ስለዚህ እንድትፈወሱ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ እያንዳንዱም ለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ብዙ ውጤት የሚያስገኝ ታላቅ ኀይል አለው፤