ዘፍጥረት 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም በሴኬም ወደሚገኘው ቅዱስ ስፍራ ወደ ሞሬ ዛፍ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ፤ በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚያች ምድር ይኖሩ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራም ትልቁ የሞሬ ዛፍ እስከሚገኝበት እስከ ሴኬም ድረስ በምድሪቱ ዘልቆ ሄደ። በዚያ ጊዜ ከነዓናውያን በዚሁ ምድር ይኖሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የባሉጥ ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፥ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ። |
ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
ያዕቆብ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቊጥር አነስተኞች ነን፤ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”
ስለዚህም በእርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ አምጥተው ለያዕቆብ ሰጡት፤ እንዲሁም በየጆሮአቸው አድርገውት የነበረውን ጒትቻ ሁሉ አውልቀው ሰጡት፤ እርሱም ሁሉንም ወሰደና በሴኬም አጠገብ በነበረው የወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።
የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን የሴኬምን ከተማ ምሽግ አድርጎ በዚያ ለጥቂት ጊዜ ቈየ፤ ከዚያም በመነሣት የፐኑኤልን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራ፤
ወንበዴዎች ሰውን ለመግደል እንደሚያደቡ የካህናቱም ቡድን እንዲሁ ያደርጋል፤ ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ እንኳ እያደቡ ሰውን ይገድላሉ፤ አሳፋሪም የሆነ ወንጀል ይፈጽማሉ።
እነዚህም ተራራዎች ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምዕራብ በኩል፥ በአራባ በሚኖሩት በከነዓናውያንም ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት ከሞሬ ዛፍ አጠገብ የሚገኙ ናቸው።
ስለዚህም የንፍታሌም ይዞታ በሆነችው በኮረብታማዋ ምድር በምትገኘው በገሊላ፥ ቄዴሽ ተብላ የምትጠራውን፥ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሴኬምንና በኮረብታማው በይሁዳ ምድር ኬብሮን የምትባለው ቂርያት አርባቅን መርጠው ለዩ፤
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጡት የዮሴፍ ዐፅም በሴኬም ተቀበረ፤ ይህም ምድር ያዕቆብ የሼኬም አባት ከሆነው ከሐሞር ልጆች በአንድ መቶ ጥሬ ብር የገዛው ነበር፤ ምድሩም የሚገኘው በዮሴፍ ዘሮች የርስት ድርሻ ክልል ውስጥ ነው።
በማግስቱም ማለዳ ይሩባዓል የተባለው ጌዴዎንና ተከታዮቹ በጧት ማልደው ተነሥተው በሐሮድ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። የምድያማውያን ሰፈርም ከእነርሱ በስተሰሜን በሞሬ ኮረብታ አጠገብ በሸለቆ ውስጥ ነበር።