Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የከነዓን ልጆች በኲሩ ጺዶን፥ ተከታዩ ሔት ይባሉ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከነዓንም፦ የበኵር ልጁ የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የከነዓን ልጆች በኲሩ ጺዶን፥ ተከታዩ ሔት ይባሉ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 10:15
18 Referencias Cruzadas  

የሚስቱ አስከሬን ካለበት ስፍራ ተነሥቶ ወደ ሒታውያን ሄደና፥


ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤


“ዛብሎን በባሕር ዳር ይኖራል፤ ወደቡም የመርከቦች ማረፊያ ይሆናል፤ የመኖሪያውም ወሰን እስከ ሲዶና ይደርሳል።


ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ።


ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤


የከነዓን የበኲር ልጅ ጺዶን ሲሆን እንዲሁም ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ ሒዋውያን፥ ዓርቃውያን፥ ሲናውያን፥ አርዋዳውያን፥ ጸማራውያንና ሐማታውያን የከነዓን ልጆች ናቸው።


እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።


ዛሬ ለእናንተ የምሰጠውን ሕግ ጠብቁ፤ እኔም አሞራውያንን፥ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ አባርራለሁ፤


የሲዶና ከተማ ሆይ! አንቺ በባሕር አጠገብ የተገነባሽ ጠንካራ ምሽግ ነሽ፤ ነገር ግን አንቺ ባል አግብታ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልዳ እንዳላሳደገች ሴት የተዋረድሽ ትሆኚአለሽ።


ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።


ቀዛፊዎችሽ ሲዶናና አርዋድ ከተባሉ ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ጢሮስ ሆይ! ባለሙያዎችሽ የመርከብ አዛዦችሽ ነበሩ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ሲዶና መልሰህ በእርስዋ ላይ ትንቢት ተናገር፤


እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በእነርሱ ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረጋቸው፤ እስራኤላውያንም መተው በሰሜን እስከ ሚስረፎትማይምና እስከ ታላቂቱ ሲዶና፥ በምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ ሳይተርፍ ሁሉንም ፈጁአቸው።


ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos