“ይህን ስጦታ በፈቃደኛነት መስጠት እንችል ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? ሁሉ ነገር ከአንተ የተቀበልነው ስጦታ ነው፤ እነሆ የአንተ የነበረውንም መልሰን ሰጥተንሃል፤
ዘዳግም 16:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም እግዚአብሔር አምላክህ በሰጠህ በረከት መጠን የበጎ ፈቃድ መሥዋዕትህን በማቅረብ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የመከር በዓል አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን፣ የእጅህን የበጎ ፈቃድ ስጦታ በማቅረብ የሰባቱ ሱባዔ የመከር በዓል አምላክህን እግዚአብሔርን አክብር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ጌታ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን፥ በፈቃድህ የምታመጣውን ስጦታ በማቅረብ የመከር በዓል አምላክህ ጌታን አክብር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ እግዚአብሔር የባረከህን ያህል እጅህ መስጠት በምትችለው መጠን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሰባቱን ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር በባረከህ መጠን በፈቃድህ የምታቀርበውን አምጥተህ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሰባቱ ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ። |
“ይህን ስጦታ በፈቃደኛነት መስጠት እንችል ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው? ሁሉ ነገር ከአንተ የተቀበልነው ስጦታ ነው፤ እነሆ የአንተ የነበረውንም መልሰን ሰጥተንሃል፤
የቤተ መቅደሱ የምሥራቃዊ በር ዘብ ጠባቂዎች አለቃ ለነበረው ለሌዋዊው ዩምና ልጅ ለቆሬ ደግሞ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን የበጎ ፈቃድ ስጦታዎች ሁሉ የመቀበልና የማከፋፈል ኀላፊነት ተሰጠው።
ምናልባት እግዚአብሔር አምላካችሁ ቊጣውን መልሶ፥ በረከቱን ይሰጣችሁ ይሆናል፤ እናንተም በዚያን ጊዜ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቊርባን ታቀርባላችሁ።
“ሴትዮዋ የበግ ጠቦት ማምጣት ካልቻለች፥ ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ታምጣ፤ እነርሱም አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ይቀርባሉ፤ ካህኑም ያስተሰርይላትና ትነጻለች፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች።”
“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።
ለወታደሮቹ ከተመደበው ክፍል፥ ከአምስት መቶ እስረኞች አንዱን፥ እንዲሁም ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ከአምስት መቶው አንዱን እጅ ለእኔ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ለዩ፤
በዚህ ጉዳይ ለእናንተ መልካም መስሎ የታየኝን ምክር እሰጣችኋለሁ፤ ባለፈው ዓመት ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ይህን ለማድረግ በመጀመሪያ የፈለጋችሁት እናንተ ነበራችሁ።
ከወንዶችና ከሴቶች ልጆችህ፥ ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮችህ በከተሞችህ ከሚኖሩት ሌዋውያን፥ በአገርህ የሚኖሩ መጻተኞች፥ እናትና አባት ከሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ሴቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት እርሱ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን በመረጠው ቦታ በአንድነት ተሰብስበህ ደስ ይበልህ።