ዳንኤል 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጊዜንና ወቅትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን በዙፋን ያስቀምጣል፣ ደግሞም ያወርዳቸዋል፤ ጥበብን ለጠቢባን፣ ዕውቀትንም ለሚያስተውሉ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፥ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፥ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። |
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ዳዊት እንዴት እንዳስተዳደረ፥ ምን ያኽል ኀይል እንደ ነበረውና በእርሱ፥ በእስራኤልና በዙሪያ ባሉት ነገሥታት ላይ ስለ ደረሰባቸው ነገር ሁሉ በእነዚሁ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል።
ሕግና ባህልን በሚመለከት ጉዳይ፥ ብልኅ አማካሪዎችን መጠየቅ በንጉሡ ዘንድ የተለመደ ነገር ስለ ነበር፥ በዚህም ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባው ይመክሩት ዘንድ አማካሪዎቹን አስጠራ።
ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ።
እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።
የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠለት፤ በራእዩም የተነገረው ቃል እውነት ነው፤ ነገር ግን ለማስተዋል እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ትርጒሙ በራእይ ተገለጠለት።
ከጥቂት ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ከሶርያ ንጉሥ ጋር የወዳጅነት ቃል ኪዳን ይመሠርታል፤ ሴት ልጁንም ለሶርያ ንጉሥ ይድርለታል፤ ነገር ግን እርስዋ ኀይልዋን ለማጠናከር ካለመቻልዋ የተነሣ የንጉሡ ኀይል ስለማይጸና የወዳጅነቱም ውል ጸንቶ አይኖርም፤ ስለዚህም እርስዋ ከደጋፊዎችዋ፥ ከልጆችዋና ከአገልጋዮችዋ ጋር ትገደላለች።
የቀድሞ አባቶቼ አምላክ ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርግሃለሁ፤ አንተ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛል፤ ጸሎታችንንም ሰምተህ የንጉሡን ሕልም ገልጠህልናል።”
ሕልሙን ልትነግሩኝ ባትችሉ ለሁላችሁም አንድ ዐይነት ቅጣት ተዘጋጅቶአል፤ ሁኔታዎች የሚለወጡ መስሎአችሁ የሐሰትና የተንኰል ቃል በመናገር ጊዜ ማራዘም ፈልጋችኋል፤ ስለዚህ ሕልሙን ብትነግሩኝ ፍቹም እንደማያስቸግራችሁ ዐውቃለሁ።”
መልአኩም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ ‘ዛፉን ቊረጡ፤ ቅርንጫፎቹንም ጨፍጭፉ፥ ቅጠሎቹን ሸምጥጡ፥ ፍሬውንም በትኑ፥ አራዊቱ ከጥላው ሥር፥ ወፎችም ከቅርንጫፎቹ ይሽሹ።
ውሳኔውም የተላለፈው በቅዱሳን መላእክት ነው፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ላይ ሥልጣን ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቅ ነው፤ ሥልጣኑንም ለፈቀደለት ሰው ይሰጠዋል፤ የተናቁትንም በሥልጣን ላይ ያስቀምጣቸዋል።’
“ንጉሥ ሆይ! ረጅምና ብርቱ የሆነው ያ ዛፍ አንተ ነህ፤ ታላቅነትህ እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ ብሎአል፤ ሥልጣንህም በዓለም ሁሉ ላይ ተንሰራፍቶአል።
ከሕዝብ መካከል ተባረህ መኖሪያህ ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ ይህም የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስክትገነዘብ ድረስ ነው።”
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
ማንኛውም ሥልጣን የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነና አሁን ያሉትም ባለሥልጣኖች የተሾሙት በእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣን መታዘዝ አለበት።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።
ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።