ዳንኤል 11:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ከጥቂት ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ከሶርያ ንጉሥ ጋር የወዳጅነት ቃል ኪዳን ይመሠርታል፤ ሴት ልጁንም ለሶርያ ንጉሥ ይድርለታል፤ ነገር ግን እርስዋ ኀይልዋን ለማጠናከር ካለመቻልዋ የተነሣ የንጉሡ ኀይል ስለማይጸና የወዳጅነቱም ውል ጸንቶ አይኖርም፤ ስለዚህም እርስዋ ከደጋፊዎችዋ፥ ከልጆችዋና ከአገልጋዮችዋ ጋር ትገደላለች። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከጥቂት ዓመታት በኋላም አንድነት ይፈጥራሉ። የደቡቡ ንጉሥ ሴት ልጅ ስምምነት ለማድረግ ወደ ሰሜኑ ንጉሥ ትሄዳለች፤ ነገር ግን ኀይሏን ይዛ መቈየት አትችልም፤ እርሱም ሆነ የርሱ ኀይል አይጸናም። በእነዚያ ቀናት እርሷ ከቤተ መንግሥት አጃቢዎቿ፣ ከአባቷና ከደጋፊዎቿ ጋራ ዐልፋ ትሰጣለች። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ከዘመናትም በኋላ ይጋጠማሉ፥ የደቡብም ንጉሥ ሴት ልጅ ቃል ኪዳን ለማድረግ ወደ ሰሜን ንጉሥ ትመጣለች፥ የክንድዋ ኃይል ግን አይጸናም፥ እርሱና ክንዱም አይጸናም፥ እርስዋና እርስዋን ያመጡ የወለዳትም በዚያም ዘመን ያጸናት አልፈው ይሰጣሉ። Ver Capítulo |