Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 31:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ማንኛውንም የእጅ ጥበብ መሥራት እንዲችል ማስተዋልና ብልኀት የማወቅም ችሎታ ይኖረው ዘንድ በመንፈሴ እንዲሞላ አድርጌአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በጥበብ፣ በብልኀት፣ ዕውቀትና ማንኛውንም ዐይነት ሙያ እንዲኖረው የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞልቼዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በጥበብ፥ በማስተዋል፥ በእውቀትና ሥራ ሁሉ እንዲሠራ የእዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በሥራ ሁሉ ያስ​ተ​ውል ዘንድ በጥ​በ​ብም፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም፥ በዕ​ው​ቀ​ትም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ፈስ ሞላ​ሁ​በት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም የእዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 31:3
12 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በትክክለኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”


ሰሎሞንም ሑራም የተባለውን ሰው ከጢሮስ ከተማ አስጠራ፤


ሑራም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሞያ ነበር፤ ቀደም ብሎ የሞተው የሑራም አባትም የጢሮስ ተወላጅ ሲሆን እርሱም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሞያ ነበር፤ የሑራም እናት የንፍታሌም ነገድ ተወላጅ ነበረች፤ ሑራም በእጅ ጥበብ ብዙ ልምድ ያለው ብልህ ሰው ነበር፤ ከንጉሥ ሰሎሞን በተደረገለት ጥሪ መሠረት መጥቶ የተመደበለትን የነሐስ ሥራ ሁሉ ሠራ።


እንግዲህ ቅርጽን የማውጣት፥ ወርቅን፥ ብርን፥ ነሐስንና ብረትን የማቅለጥ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ልብስ የመሥራት ችሎታ ያለውን ብልኀተኛ ሰው ላክልኝ፤ እርሱም አባቴ ዳዊት ከመረጣቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልኀተኞች ሰዎች ጋር ይሠራል።


እኔ ልዩ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረግኋቸውን የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችን ጠርተህ ለአሮን ልብስ እንዲሠሩለት ንገራቸው፤ በዚህ ዐይነት አሮን ካህን በመሆን ያገለግለኝ ዘንድ ለእኔ የተለየ ይሆናል።


ስለዚህም በብልኀት የሥራ ዕቅድ እያወጣ ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ ልዩ ልዩ ነገሮችን ይሠራል።


እግዚአብሔር እርሱን በመንፈሱ ኀይል እንዲሞላ አድርጎ ማናቸውንም የጥበብ ሥራ መሥራት እንዲችል ብልኀትን፥ ችሎታንና ማስተዋልን ሰጥቶታል።


በአንጥረኛ፥ በፕላን አውጪ ባለሞያ፥ ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ቀለም የተነከረ ከፈይ ሌላውንም የልብስ ሥራ በሚያከናውኑ ሸማኔዎች የተሠራውን ነገር ሁሉ ለማስጌጥ የሚችሉበትን ብልኀት ሰጥቶአቸዋል፤ እነርሱ ማናቸውንም የጥበብ ሥራ ለመሥራትና በብልኀት የሚሠራውንም ሁሉ ዕቅድ ለማውጣት የሚችሉ ናቸው።


ጥበብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም የሚገኙት ከእርሱ ዘንድ ነው።


ከአምላኩ የተማረ ስለ ሆነ ትክክለኛውን መንገድ ያውቃል።


በዳኝነት ለሚያገለግሉት የፍትሕ ጥበብ ይሰጣቸዋል፤ የከተማይቱን የቅጽር በሮች ከጠላት ለሚከላከሉትም ኀይልን ይሰጣቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos