Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 31:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህም በብልኀት የሥራ ዕቅድ እያወጣ ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ ልዩ ልዩ ነገሮችን ይሠራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ይኸውም በወርቅ፣ በብርና በንሓስ ለሚሠሩት ሥራዎች በጥበብ የተሠሩ ጌጦችን እንዲያበጅ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ልዩ ማስተዋል እንዲኖረው፥ በወርቅ፥ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የአ​ና​ጺ​ዎች አለቃ ይሆን ዘንድ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ናስ​ንም፥ ብጫና ሰማ​ያዊ፥ እጥፍ ሆኖ የተ​ፈ​ተለ ነጭና ቀይ ሐርን ይሠራ ዘንድ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የጥበብን ሥራ ያስተውል ዘንድ፥ በወርቅና በብር በናስም ይሰራ ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 31:4
8 Referencias Cruzadas  

ሑራም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሞያ ነበር፤ ቀደም ብሎ የሞተው የሑራም አባትም የጢሮስ ተወላጅ ሲሆን እርሱም ነሐስ አቅልጦ በመሥራት ጥበብ የሠለጠነ ባለሞያ ነበር፤ የሑራም እናት የንፍታሌም ነገድ ተወላጅ ነበረች፤ ሑራም በእጅ ጥበብ ብዙ ልምድ ያለው ብልህ ሰው ነበር፤ ከንጉሥ ሰሎሞን በተደረገለት ጥሪ መሠረት መጥቶ የተመደበለትን የነሐስ ሥራ ሁሉ ሠራ።


እንግዲህ ቅርጽን የማውጣት፥ ወርቅን፥ ብርን፥ ነሐስንና ብረትን የማቅለጥ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ልብስ የመሥራት ችሎታ ያለውን ብልኀተኛ ሰው ላክልኝ፤ እርሱም አባቴ ዳዊት ከመረጣቸው በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት ብልኀተኞች ሰዎች ጋር ይሠራል።


“እንዲሁም የተቀደሰውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች አብጀው፤ በእነርሱም ላይ ኪሩቤል በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ።


“የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጠየቅበትን የደረት ኪስ ለሊቀ ካህናቱ ሥራ፤ አሠራሩ እንደ ኤፉድ ሆኖ በተመሳሳይ ጥልፍ ያጌጠ ይሁን።


ማንኛውንም የእጅ ጥበብ መሥራት እንዲችል ማስተዋልና ብልኀት የማወቅም ችሎታ ይኖረው ዘንድ በመንፈሴ እንዲሞላ አድርጌአለሁ፤


እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን ድንጋይ ለመቅረጽ፥ እንጨትንም ለመጥረብ፥ ሌላውንም ሥራ ሁሉ በጥበብ ለማከናወን እንዲችል አድርጌዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos