2 ቆሮንቶስ 8:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእምነት፥ በንግግር፥ በዕውቀት፥ በትጋት፥ ለእኛም ባላችሁ ፍቅር በሁሉ ነገር ትበልጣላችሁ፤ በዚህ በልግሥና ሥራም እንድትበልጡ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም በሁሉ ነገር ይኸውም በእምነት፣ በቃል፣ በዕውቀት፣ በፍጹም ትጋትና ለእኛም ባላችሁ ፍቅር ልቃችሁ እንደ ተገኛችሁ፣ በዚህም የቸርነት ሥራ ልቃችሁ እንድትገኙ ዐደራ እንላችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነት፥ በቃል፥ በእውቀት፥ በትጋት፥ እንዲሁም ለእኛ በፍቅራችሁ ልቃችሁ እንደተገኛችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ልቃችሁ ተገኙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁሉ ነገር በእምነትና በቃል፥ በዕውቀትም፥ በትጋትም በእናንተ ዘንድ በሆነው ሁሉ እኛን በመውደዳችሁ ፍጹማን እንደ ሆናችሁ፥ እንዲሁም ደግሞ ይህቺን ስጦታ አብዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነትና በቃል በእውቀትም በትጋትም ሁሉ ለእኛም በፍቅራችሁ እንደ ተረፋችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ትረፉ። |
አይሁድም ብንሆን የግሪክ ሰዎች ብንሆን፤ ባሪያዎችም ብንሆን፥ ነጻ ሰዎችም ብንሆን፥ አንድ ሰውነት ለመሆን በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀናል፤ ሁላችንም ከዚሁ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተናል።
ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝና ምሥጢርንም ሁሉ ብረዳ፥ ዕውቀትም ሁሉ ቢኖረኝ፥ ተራራን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያፈልስ እምነትም ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።
ፍቅር ያለው ሰው ምንጊዜም አይወድቅም፤ ትንቢትን የመናገር ስጦታ ያልፋል፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ያልፋል፤ ዕውቀትም ቢሆን ያልፋል።
እናንተም የመንፈስ ቅዱስን ስጦታዎች በብርቱ ስለምትሹ በይበልጥ መፈለግ የሚገባችሁ ክርስቲያኖች የሚታነጹባቸው ስጦታዎች እንዲበዙላችሁ ነው።
አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ?
የተጽናናነውም በእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተ እርሱን ያጽናናችሁት መሆኑን በመስማታችንም ጭምር ነው፤ ስለ እኔ ያላችሁን ናፍቆትና ሐዘን ጭንቀትም በነገረን ጊዜ ይበልጥ ደስ አለኝ።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ምክንያት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ማመስገንም ተገቢያችን ነው፤ የምናመሰግነውም እምነታችሁ ይበልጥ እያደገና የእያንዳንዳችሁ የእርስ በርስ ፍቅር እየጨመረ በመሄዱ ነው።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
ይልቅስ በጌታችንና በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እርሱንም በማወቅ ከፍ ከፍ በሉ፤ ለእርሱ አሁንም ለዘለዓለምም ክብር ይሁን! አሜን።
‘እኔ ሀብታም ነኝ፤ ብዙ ሀብት አለኝ፤ የሚጐድለኝ ምንም የለም’ ትላለህ፤ ነገር ግን ጐስቋላ፥ ምስኪን፥ ድኻ፥ ዕውርና የተራቈትህ መሆንክን አታውቅም፤