ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ሰቈቃወ 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአጠገብሽ የሚያልፉ ሁሉ፣ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፤ “የውበት መደምደሚያ፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣ የተባለች ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ ራሳቸውን በመነቅነቅ፣ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያሾፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ፍጹም ውብ ናት የሚሏት የዓለም መደሰቻ የነበረችው ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እጃቸውን እያጨበጨቡ ራሳቸውን በመነቅነቅ አሽሟጠጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳምኬት። መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፦ “በውኑ የምድር ሁሉ ደስታ፥ አክሊልና ክብር የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ። |
ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ፦ ‘ጌታ በዚህ አገርና በዚህ ቤት ለምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ።
ጌታም፥ በፐራሲም ተራራ እንዳደረገው፥ በገባዖንም ሸለቆ እንዳደረገው፥ ሥራውን ለመሥራት፥ አስደናቂ ሥራውን! ተግባሩን ለመፈጸም፥ አስገራሚ ተግባሩን! ይነሣል፤ ይነሣሣልም።
ጌታ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ስትሸሽ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ባድማና መሣቀቂያ ማፍዋጫም እርግማንም ላደርጋቸው፥ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ነገሥታትዋንም አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
እነሆ፥ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እልካለሁ ይላል ጌታ፥ ባርያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፥ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመሣቀቂያና ለማፍዋጫም ለዘለዓለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
በሰይፍም በራብም በቸነፈርም አሳዳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድኋቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል ለመረገሚያና ለመሣቀቂያ ለማፍዋጫም ለመሰደቢያም ይሆናሉ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፥ የሚያጽናናኝ የለም፥ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፥ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፥ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ ረክሳለች፥ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፥ እርሷም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች።
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ።
ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቁጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ።
በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፥ ሐርና ወርቀዘቦ ነበር፥ የላመ ዱቄት፥ ማርና ዘይትም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ፥ ለንግሥትነትም በቃሽ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእስራኤል ምድር ላይ በውስጥሽ ባለው ንቀት ሁሉ ደስ ብሎሽ በእጅሽ አጨብጭበሻልና፥ በእግርሽም አሸብሽበሻልና፥
በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።
የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።
ስብራትህን የሚያሽል የለም፥ ቁስልህ የከፋ ነው፤ ወሬህን የሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፤ የማያቋርጥ ክፋትህ ያላለፈበት ማን ነውና?
ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።
በመንገድ የሚያልፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ የስድብ ናዳ በማውረድ እንዲህ ይሉት ነበር፤ “አይ፥ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራ አንተ ነህ፤