ሕዝቅኤል 16:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፥ ሐርና ወርቀዘቦ ነበር፥ የላመ ዱቄት፥ ማርና ዘይትም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ፥ ለንግሥትነትም በቃሽ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ያማረ በፍታ፣ ሐርና ወርቀ ዘቦ ነበር፤ ምግብሽም የላመ ዱቄት፣ ማርና የወይራ ዘይት ነበር። እጅግ ውብ ሆንሽ፤ ንግሥት ለመሆንም በቃሽ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ብዙ ጌጣጌጦች ነበሩሽ፤ ከልዩ ልዩ ሐር የተሠሩና በጥልፍ ጌጥ የተዋቡ ውድ ልብሶች ነበሩሽ፤ ምርጥ ከሆነ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ፥ ማርና የወይራ ዘይት ትመገቢ ነበር፤ ውበትሽ እጅግ እየጨመረ ስለ ሄደ ንግሥት ለመሆን በቃሽ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፤ ልብስሽም ጥሩ በፍታና ሐር፥ ወርቀ ዘቦም ነበረ፤ አንቺም መልካምን ዱቄትና ማርን፥ ዘይትንም በላሽ፤ ወፈርሽ፤ እጅግም ውብ ሆንሽ፤ ለመንግሥትም የተዘጋጀሽ አደረግሁሽ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታና ሐር ወርቀ ዘቦም ነበረ፥ አንቺም መልካም ዱቄትና ማርን ዘይትንም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ ለመንግሥትም ደረስሽ። Ver Capítulo |