በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ኤርምያስ 15:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤ ታገለግለኛለህም፤ የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣ አፍ ትሆነኛለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣ አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ወደ እኔ በንስሓ ብትመለስ፥ እቀበልሃለሁ፤ እንደገናም አገልጋይ ትሆነኛለህ፤ ከንቱ ቃል መናገርህን ትተህ ቁም ነገር ያለውን መልእክት ብታስተላልፍ፥ እንደገና የእኔ ነቢይ ትሆናለህ፤ ሕዝቡ ወደ አንተ ይመጣሉ እንጂ አንተ ወደ እነርሱ አትሄድም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፤ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ በፊቴም ትቆማለህ፥ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፥ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፥ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም። |
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።
ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እየጮኹ ያለቅሳሉ እንጀራም ይፈልጋሉ፥ ሰውነታቸውን ለማበርታት የከበረ ሀብታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፥ አቤቱ፥ ተጐሳቁያለሁና እይ፥ ተመልከትም።
ካህናቶችዋም ሕጌን ጥሰዋል፥ ቅዱሳት ነገሮቼንም አርክሰዋል፤ ቅዱስ በሆነ ነገርና በረከሰ ነገር ላይ ልዩነትን አላደረጉም፥ በርኩስ ነገርና በንጹሕ ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አላስታወቁም፥ ከሰንበቶቼ ዓይናቸውን ሰወሩ፥ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።
አሁን ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሳምናለሁን? ወይስ ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? እስከ አሁን ሰውን ደስ የማሰኝ ብሆን ኖሮ የክርስቶስ ባርያ አልሆንም ነበር።