ኤርምያስ 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ፥ እኔን ትተውኛል፤ ለሌሎችም አማልክት ዕጣንን አጥነዋል፤ ለእጃቸውም ሥራዎች ሰግደዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔን በመተው ክፋት ስለ ሠሩ፣ ለሌሎች አማልክት ዕጣን ስላጠኑ፣ እጆቻቸው የሠሯቸውን ስላመለኩ፣ በሕዝቤ ላይ ፍርድን ዐውጄአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ኃጢአት ስለ ሠሩ እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ እኔን ትተው ለሌሎች አማልክት ዕጣን ያጥናሉ፤ ምስሎችንም ሠርተው ይሰግዱላቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ክፋታቸውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተዉ፥ ለሌሎችም አማልክት ስለ ሠዉ፥ ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ክፋታቸውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተዉ ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ። |
አሳንም ሊያገኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከጌታ ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል።
“እናንተ ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ሥርዓቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥
ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፤ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል።
ለበዓልም በማጠናቸው አስቈጡኝ፥ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
አንቺ እኔን ትተሺኛል፥ ይላል ጌታ፥ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጥፍቼሻለሁ፤ ይቅርታን ከማድረግ ደክሜአለሁ።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤
ሕዝቤ ግን ረስተውኛል ለከንቱ ነገርም ዐጥነዋል፤ ከመንገዳቸውም አሰናክለዋቸዋል ከቀድሞውም ጐዳና ርቀው ወዳልተሠራው ወደ ጠማማው መንገድ ሄደዋል።
ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም የይሁዳም ነገሥታት ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነውበታልና፤ እነርሱም ይህን ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታልና፥
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን ሠርቷል፤ እኔን የሕይወት ውኃ ምንጭን ትተውኛል፥ ውኃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጉድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።
ነገር ግን እኛና አባቶቻችን ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ እንዳደረግነው፥ ለሰማይ ንግሥት ለማጠን የመጠጥንም ቁርባን ለእርሷ ለማፍሰስ ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን፤ በዚያን ጊዜም እንጀራ እንጠግብ ነበር፥ መልካምም ይሆንልን ክፉም አናይም ነበር።
ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።
እኔን ለማስቆጣት፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ፥ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ፤ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቁርባን ያፈስሳሉ።
ትሰርቃላችሁን፥ ትገድላላችሁን፥ ታመነዝራላችሁን፥ በሐሰትም ትምላላችሁን፥ ለበዓልም ታጥናላችሁን፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁን፤
እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፤ ይፈፀማል፥ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልቆጠብም፥ አልራራም፥ አልጸጸትም። እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽ ይፈርዱብሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ያሰማል፥ ሠራዊቱ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚፈጽም እርሱ ኃያል ነውና፥ የጌታ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?
“እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈጸምህ የተነሣ፥ እስክትደመሰስ ፈጥነህም እስክትጠፋ ድረስ እጅህ በነካው ሁሉ ላይ ጌታ ርግማንን፥ ሁከትንና መደናገርን ይልክብሃል።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።
በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ ለአጋንንትና ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶችም መስገድን አልተዉም።