Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 37:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ፥ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አማልክታቸውን ወደ እሳት ጥለዋል፤ በሰው እጅ የተቀረጹ የድንጋይና የዕንጨት ምስሎች እንጂ አማልክት አልነበሩምና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንጨቱን በመጥረብ፥ ድንጋዩን በማለዘብ በሰው እጅ የተሠሩ ከንቱ የሆኑ አማልክታቸውን በእሳት አቃጥለው አጥፍተዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፥ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 37:19
25 Referencias Cruzadas  

የተሠራው ነገር ከእስራኤል ዘንድ ነው፤ እርሱም በሞያተኛ የተሠራ ነው፤ እርሱም አምላክ አይደለም፤ የሰማርያም እምቦሳ ይሰባበራል።


እናንተም፦ “ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ” ትሉአቸዋላችሁ።


የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግድበታል፤ ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።


እነሆ፥ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ ሥራቸውም ምንም ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ባዶ ነፋስ ናቸው።


እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው።


አናጢውም አንጥረኛውን፥ በመዶሻም የሚያሳሳውን በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያጽናናዋል፥ ስለ ብየዳ ሥራውም፦ “መልካም ነው” ይለዋል፤ እንዳይላቀቅም በችንካር ያጋጥመዋል።


እነርሱ ሞተዋል፥ በሕይወት አይኖሩም፤ ጠፍተዋል፥ አይነሡም፤ ስለዚህ አንተ ጎብኝተሃቸዋል፤ አጥፍተሃቸውማል፤ መታሰቢያቸውንም ሁሉ እንዳልነበር አድርገሃል።


ፍልስጥኤማውያንም ጣዖቶቻቸውን ትተው ሸሹ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው።


የሠሩትን ጥጃ ወስዶ በእሳት አቀለጠው፥ እስኪደቅም ድረስ ፈጨው፥ በውኃውም ላይ በተነው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲጠጡት አደረገ።


ነገር ግን ቀድሞ እግዚአብሔርን ሳታውቁ፥ በተፈጥሮአቸው አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ነበር፤


ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸው ላበጇቸው፤ ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ።


በእጃቸውም ወደ ሠሯቸው መሠዊያዎች አይመለከቱም፤ በጣቶቻቸው ወዳበጇቸው የዕጣን መሠዊያዎች ወይም ወደ ማምለኪያ ዐምዶች አይመለከቱም።


ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ፥ እኔን ትተውኛል፤ ለሌሎችም አማልክት ዕጣንን አጥነዋል፤ ለእጃቸውም ሥራዎች ሰግደዋልና።


በውኑ አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ክብሩን በማይረባ ነገር ለወጠ።


በውኑ ሰው አማልክት ያልሆኑትን ለራሱ አማልክት አድርጎ ይሠራልን?”


እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፤ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios