እነርሱም፦ ‘ወዴት እንውጣ?’ ቢሉህ፥ አንተ፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ’ ትላቸዋለህ።
ሕዝቅኤል 28:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርሷ ላይ መቅሠፍት አመጣለሁ፤ በመንገዶቿ ላይ ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ ከየአቅጣጫው በሚመጣ ሰይፍ፣ የታረዱት በውስጧ ይወድቃሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅሠፍቴን በእናንተ ላይ አመጣለሁ፤ በየመንገዱም ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ በየአቅጣጫው በሚነሣባችሁ ጦርነት ምክንያት በመካከላችሁ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሕዝቦችም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቸነፈርንም በአንቺ ላይ፥ ደምንም በጎዳናሽ ላይ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያሽም በላይሽ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልሽ ይወድቃሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቸነፈርንም በእርስዋ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፥ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። |
እነርሱም፦ ‘ወዴት እንውጣ?’ ቢሉህ፥ አንተ፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ’ ትላቸዋለህ።
አንተም የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር፥ መዳፍህን በመዳፍህ ምታ፥ የተገደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደጋግም የሚከብባቸው የተገደለ የታላቅ ሰው ሰይፍ ነው።
ስለዚህ እነሆ እጄን በአንተ ላይ ዘርግቻለሁ፥ እንዲበዘብዙህ ለሕዝቦች እሰጥሃለሁ፥ ከሕዝቦች እቆርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም እደመስስሃለሁ፤ አጠፋሃለሁም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ።
የሰሜን አለቆች ሁሉ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኃይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሃት አፍረዋል፥ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱት ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።
በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍና የበረዶ ድንጋይ፥ እሳትና ዲን በእርሱና በወታደሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉት ብዙ ሕዝቦች ላይ አዘንባለሁ።
ከአንቺም አንድ ሦስተኛው በቸነፈር ይሞታሉ፥ በመካከልሽም በራብ ያልቃሉ፥ አንድ ሦስተኛውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ አንድ ሦስተኛውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ፥ በኋላቸውም ሰይፍ እመዝዛለሁ።
ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆችሽን ያሳጡሻል፥ ቸነፈርና ደምም በአንቺ በኩል ያልፋሉ፥ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።