Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 32:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የሰሜን አለቆች ሁሉ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኃይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሃት አፍረዋል፥ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱት ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “የሰሜን ገዦች በሙሉ፣ ሲዶናውያንም ሁሉ በዚያ ይገኛሉ፤ ከዚህ በፊት በኀይላቸው ምክንያት ሽብር የፈጠሩ ቢሆኑም፣ ከታረዱት ጋራ በኀፍረት ወረዱ፤ ሳይገረዙም በሰይፍ ከተገደሉት ጋራ ይጋደማሉ፤ ወደ ጕድጓድ ከወረዱትም ጋራ ኀፍረታቸውን ይሸከማሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 “የሰሜን መሳፍንትና ሲዶናውያን እዚያ ናቸው፤ በሥልጣናቸው ተመክተው ሽብር ቢነዙም እንኳ ከተገደሉት ጋር በውርደት ወደ ሙታን ዓለም ወርደዋል፤ በሰይፍ ተገድለው ኀፍረታቸውን በመከናነብ ከወረዱት ጋር በእግዚአብሔር ሳያምኑ ተጋድመዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከአ​ል​ተ​ገ​ረ​ዙና ወደ ጕድ​ጓድ ከሚ​ወ​ርዱ ጋር ተኝ​ተ​ዋል፤ የሰ​ሜን አለ​ቆች ሁሉ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ወር​ደው በዚያ አሉ፤ በኀ​ይ​ላ​ቸ​ውም ያስ​ፈሩ በነ​በ​ረው ፍር​ሀት አፍ​ረ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ከተ​ገ​ደ​ሉት ጋር ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ተኝ​ተ​ዋል፤ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ጋር ቅጣ​ታ​ቸ​ውን ተሸ​ክ​መ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የሰሜን አለቆች ሁሉ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፥ በኃይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሃት አፍረዋል፥ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ሳይገረዙ ተኝተዋል፥ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 32:30
11 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ እኔ በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እነርሱም ይመጣሉ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም በር መግቢያ በዙሪያዋም ባለ ቅጥርዋ ሁሉ ላይ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ።


የጤሮስን ነገሥታትም ሁሉ፥ የሲዶናን ነገሥታትም ሁሉ፥ በባሕር ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትንም፥


አንዱን ከሌላው በመቀጠል፥ ቅርብና ሩቅ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፥ በምድር ፊት ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታትንም ሁሉ አጠጣኋቸው፤ የሼሻክም ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።


የጥንት ሕዝብ ወዳሉበት ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፥ የሚኖርብሽም እንዳይገኝ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ቀድሞ በፈረሰችው ስፍራ፥ በታችኛይቱ ምድር አኖርሻለሁ፤ ጌጥሽንም በሕያዋን ምድር አላኖርም።


በባዕዳን እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ሲዶና አቅንተህ ትንቢት ተናገርባት፥ እንዲህም በል፦


ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


በስተ ሰሜን ርቆ ከሚገኘው ስፍራህ አንተ፥ ከአንተም ጋር ሁሉም በፈረሶች ላይ የተቀመጡ ብዙ ሕዝብ፥ ታላቅ ጉባኤና ብርቱ ሠራዊት ጋር ሆነህ ትመጣለህ።


ጎሜርንና ሠራዊቱ ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻ ያለው የቶጋርማ ቤትና ሠራዊቱ ሁሉ፥ ብዙ ሕዝቦችም ከአንተ ጋር አወጣለሁ።


እመልስሃለሁ፥ እመራሃለሁ፥ ከሰሜን ዳርቻ አወጣሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች እወስድሃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos