Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆችሽን ያሳጡሻል፥ ቸነፈርና ደምም በአንቺ በኩል ያልፋሉ፥ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ራብንና የዱር አራዊትን እሰድድባችኋለሁ፤ እነርሱም ልጅ አልባ ያደርጓችኋል። ቸነፈርና ደም መፋሰስ ያጥለቀልቃችኋል፤ ሰይፍንም አመጣባችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ራብንና የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይገድላሉ፤ ጦርነትንም አመጣባችኋለሁ፤ መቅሠፍትና ግድያም በመካከላችሁ ይስፋፋል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ራብ​ንና ክፉ​ዎ​ችን አራ​ዊት እሰ​ድ​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እቀ​ሥ​ፍ​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም ያጠ​ፋሉ ቸነ​ፈ​ርና ደምም በአ​ንቺ ላይ ይመ​ጡ​ብ​ሻል፤ ሰይ​ፍ​ንም አመ​ጣ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻ​ልም። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድባችኋለሁ፥ ልጆቻችሁንም ያጠፋሉ፥ ቸነፈርና ደምም በአንቺ ዘንድ ያልፋሉ፥ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 5:17
28 Referencias Cruzadas  

እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር። ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፤


ምድሪቱ ባድማ እንዳትሆን፥ የምድር አራዊትም እንዳይበዙብህ፥ በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም።


ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ ዐራቱን ዓይነት ጥፋት ልኬባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።


ክፉ አውሬ በምድሪቱ እንዲያልፍ ባደርግ፥ ልጅ አልባ ቢያደርጋት፥ በአውሬው ምክንያት ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥


ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ ቁጣዬን በደም ባፈስስባትና ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ ባጠፋ፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥


የሚያመልጡ ወታደሮቹ ሁሉ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ የቀሩትም ሁሉ ወደ እየነፋሳቱ ይበተናሉ፥ እኔም ጌታ እንደ ተናገርሁ ታውቃላችሁ።


የዱር ዛፎች ሁሉ ረጅሙን ዛፍ ዝቅ ያደረግሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ ያደረግሁ፥ የለመለመውንም ዛፍ ያደረቅሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ ያለመለምሁ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ እኔም አደርጋለሁ።


ለእስራኤልም ምድር እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ሰይፌን ከሰገባው እመዝዘዋለሁ፥ ጻድቁንና ክፉውን ከአንቺ ዘንድ አስወግዳለሁ።


ለእሳት ማገዶ ትሆናለህ፥ ደምህም በምድር መካከል ይሆናል፥ ደግሞም አትታሰብም፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁና።


ከአንቺ ጋር በምነጋገርበት ጊዜ ልብሽ መቋቋም ይችላልን? እጆችሽስ ይጸናሉን? እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ፥ አደርገዋለሁም።


ጉባኤውም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል፥ በሰይፋቸው ይቆርጡአቸዋል፤ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።


የተራቆተ ዓለት አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ትሆኛለሽ፤ ዳግምም አትሠሪም፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ወንዞችን አደርቃለሁ፥ ምድሪቱን በክፉ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ፥ ምድሪቱንና ሞላዋን በባዕዳን እጅ ባድማ አደርጋለሁ፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁ።


እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በፍርስራሽ ስፍራዎች ያሉት በሰይፍ ይወድቃሉ፥ በሜዳ ያሉትን መብል እንዲሆን ለአራዊት እሰጠዋለሁ፥ በምሽጎችና በዋሻዎች ያሉት በቸነፈር ይሞታሉ።


መንፈሴን በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁ አስቀምጣችኋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደ ተናገርሁ፥ እንዳደረግሁትም ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ።


በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፤ ዶፍና የበረዶ ድንጋይ፥ እሳትና ዲን በእርሱና በወታደሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉት ብዙ ሕዝቦች ላይ አዘንባለሁ።


በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።


የሚገድሉና የሚያጠፉ የራብ ፍላፃ በወረወርሁ ጊዜ፥ እንዳጠፋችሁ እወረውራቸዋለሁ፥ በእናንተ ላይ ረሃብን እጨምርባችኋለሁ፥ የምግባችሁንም በትር እሰብራለሁ።


የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦


በሩቅ ያለው በቸነፈር ይሞታል፥ በቅርብ ያለውም በሰይፍ ይወድቃል፥ በሕይወት የተረፈውና የዳነውም በራብ ይሞታል፥ መዓቴን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።


በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


በሚያቃጥል ንዳድና በራብ ያልቃሉ፤ በወረርሽኝ መቅሠፍት ይጠፋሉ፤ ተናካሽ አውሬዎችን፥ ከሚሳቡ መርዘኛ እባቦችን ጋር እሰድባቸዋለሁ።


አየሁም፤ እነሆም የገረጣ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos